አገርአቀፍ የውሃና ኢነርጂ ኤግዚቢሽን መስከረም 10/2016 ዓ.ም ተጠናቋል።

የውሃ ሀብታችን ለብልጽግናችን” በሚል መርህ በኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና በአረብ ኤምሬትስ ፕሬዚዳንት ክቡር ሸህ መሀመድ ቢን ዛይድ ነሐሴ 12/2015 ዓ.ም. በይፋ የተከፈተው አገርአቀፍ የውሃና ኢነርጂ ኤግዚቢሽን መስከረም 10/2016 ዓ.ም ተጠናቋል። በኤግዚቢሽኑ ከሚቲዮሮሎጅ አገልግሎት ጋር ተያይዞ እየተተገበሩ ያሉ ቴክኖሎጂዎች፣ የዲጂታል የአሰራር ሂደቶችና ልዮ ልዮ የዘርፉ ክንዋኔዎች ቀርበዋል። በውሃ ሀብት አስተዳር ዘርፍም ጥቅም ላይ የዋሉ ቴክኖሎጅዎችና የዲጅታል ትግበራዎየች ቀርበው ተጎብኝተዋል። በሌላ በኩል በመጠጥ ዉሃ አቅርቦትና በሳኒቴሽን አገልግሎት ዘርፉን ለማዘመን እየተተገበሩ ያሉ ቴክኖሎጅዎችና የዲጅታል ምርቶች ታይተዋል። በዘርፉ እየተከናወኑ የሚገኙ ከአቅም ግንባታና ከቴክኖሎጅ ሽግግር ጋር የተያያዙ ስራዎችም ተጎብኝተዋል። በኢነርጂ ልማት ዘርፍ ደግሞ ልዩ ልዩ የቴክኖሎጅ ውጤችች የዲጅታል አሰራሮች ቀርበው ተጎብኝተዋል። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሞዴል ቨርቹዋል ሪያሊቲ ሾው የኤግዚቢሽኑ ድምቀቶች ነበሩ። በመጨረሻም ይህ ኤግዚቢሺን እንዲሳካ አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ ተቋማት፤ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት፣ ሳይንስ ሙዚየም፣ ኢቲዮ ቴሌኮም፣ ዋፋ ማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን፣ የሚኒስቴሩ ተጠሪ ተቋማት፣ አጋር ድርጅቶች ተሳታፊ የነበራችሁ የንግድ ድርጆቶች ላቅ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ በአስተባባሪነት የተሳተፋችሁ፣ በአስረጂነት የተሳተፋችሁ፣ በልዩ ልዩ አገልግሎት የተሳተፋችሁ የከበረ ምስጋናችንን እንገልጻለን፡፡ ከፌደራል ተቋማት የጎበኛችሁ፤ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክፍለ ከተሞችና ከልዩ ልዩ አደራጃጀቶች መጥታችሁ የጎበኛችሁ፤ ከሸገር ሲቲ ክፍለከተሞች ተገኝታችሁ የጎበኛችሁ፤ ከክልሎችና በልዩ ልዩ ሁኔታ መጥታችሁ የጎበኛችሁ ላቅ ያለ ምስጋናችንን እንገልጻለን፡፡ በመጨረሻም በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀው ኤግዚቢሽን ቢጠናቀቅም፤ በቀጣይ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ግቢ ውስጥ አዲስ በተገነባው ዲጂታል ኤግዚቢሽን አማካኝነት እንደሚቀጥል መግለጽ እንወዳለን፡፡ በቅርብ ቀናት የማጠቃለያ መርሃግብር እንደምናካሂድ እንገልጻለን፡፡

Share this Post