"ሀገራችን በዚህ ደረጃ በቴክኖሎጂው አድጋለች ብዬ አልገመትኩም"
የ1ኛና የ2ኛ ደረጃ ት/ት ቤት ተማሪዎች
መስከረም 08/2016 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) "የውሃ ሀብታችን ለብልፅግናችን!" በሚል መርህ የተዘጋጀው የውሃና ኢነርጂ አውደርእይን የቅድስት ስላሴ 2ኛ ደረጃ ት/ት ቤት፣ የዳግማዊ ሚኒሊክ 2ኛ ደረጃና የጆን ኦፍ ኬኔዲ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ት ቤት ተማሪዎች ጎበኙ።
ከጉብኝቱ በኋላ አውደርእዩን አስመልክቶ ተማሪዎች የተለያየ አስተያየት የሰጡ ሲሆን "ሀገራችን በዚህ ደረጃ በቴክኖሎጂው አድጋለች ብዬ አልገመትኩም ነበር" ያለው ተማሪ የደመና ማበልፀግና የሚቲዎሮሎጂ የመረጃ አያያዝ ስርአት እኛንም ወደፈጠራ ስራ እንድንሰማራ የሚያነሳሳ ነው ሲል አስተያየት ሰጥቷል።
በሌላ በኩል ያነጋገርናት የ1ኛ ደረጃ ተማሪ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እዚህ ደረጃ ደርሶ ማየታች አስደስቶናል፤ በቀጣይም እንደተማሪ የሚጠበቅብንን አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ ነን ስትል ተናግራለች።
በቀሩት ጥቂት ቀናት ውስጥ ይምጡና ይጎብኙ!