ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው የዓለም ባንክ ልዑክን ተቀብለው አነጋገሩ

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው የዓለም ባንክ ልዑክን ተቀብለው አነጋገሩ

ነሐሴ 18/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ፣ በዓለም ባንክ የመሠረተ ልማት ቀጠናዊ ዳይሬክተር ሚስተር ኤሪክ ማግነስ ፈርንስትሮም የሚመራውን ልዑክ በቢሯቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

በውይይቱም በኢትዮጵያ የኢነርጂ ዘርፍ የልማት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች፣ በሂደት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች እና የሁለቱን አካላት ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተመካከሩ።

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው የዓለም ባንክ በኢነርጂ ዘርፍ እያደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀው፤ ባለፉት አምስት ዓመታት በመንግሥትና በልማት አጋር አካላት የተደረገ የገንዘብ ድጋፍ በርካታ የኢነርጂ ልማት ሥራዎችን ለማከናወን እንዳስቻለና ህብረተሰቡን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ የተጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።

በቀጣይም የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን አስተማማኝና ዘላቂ በሆነ መልኩ ለማስፋት የግሉን ዘርፍ ኢንቨስትመንት ለመሳብ እየተሠራ መሆኑን ገልፀው፣ የዓለም ባንክ በተቋሙ በሚተገበሩ የኢነርጂ ፕሮጀክቶች የፋይናንስ ድጋፉን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።

ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተደራሽነቷን ለማሳደግ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ፍላጎት በመኖሩ የኢነርጂ ፖሊሲው መከለሱንም ሚኒስትር ዴኤታው ጠቁመዋል።

የዓለም ባንክ የመሠረተ ልማት ቀጠናዊ ዳይሬክተር ሚስተር ኤሪክ ፈርንስትሮም በበኩላቸው በኢነርጂ ዘርፍ ያለው ትብብር በተቀናጀ መልኩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው፤ በቀጣይ በልማት ፕሮጀክቶች፣ በተቋማዊ ማሻሻያዎችና በግሉ ዘርፍ ተሳትፎ የኢነርጂ ዘርፉን ዘላቂ ልማት ለማጠናከር ከሚኒስቴሩ ጋር በትብብር ለመሥራት ቁርጠኝነታቸውን ገልፀዋል።

በውይይቱ የሚኒስቴሩ የሥራ ኃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።

ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ

https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/

ቴሌግራም

http://t.me/mowieethiopia

ዌብሳይት

http://mowe.gov.et

X/ትዊተር

https://x.com/mowe_ethiopia

ዩቱዩብ

https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s

ቲክቶክ

tiktok.com/@mowetikto

Share this Post