የጎርፍ አደጋን ለመቀነስ የኢንቨስትመንት ሥራዎች የአዋጭነት ጥናት፣ ዝርዝር ዲዛይንና የጨረታ ሰነድ ዝግጅት የግምገማ ወርክሾፕ ተካሄደ
የጎርፍ አደጋን ለመቀነስ የኢንቨስትመንት ሥራዎች የአዋጭነት ጥናት፣ ዝርዝር ዲዛይንና የጨረታ ሰነድ ዝግጅት የግምገማ ወርክሾፕ ተካሄደ
አርባምንጭ፣ ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም. (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ጎርፍ መከላከል ፕሮጀክት አዘጋጅነት በስምጥ ሸለቆ ሐይቆችና በኦሞ–ጊቤ ወንዝ ተፋሰሶች የጎርፍ አደጋን ለመቀነስ የታቀዱ የኢንቨስትመንት ሥራዎች የአዋጭነት ጥናት፣ ዝርዝር ዲዛይንና የጨረታ ሰነድ ዝግጅት የግምገማ ወርክሾፕ በአርባምንጭ ሀይሌ ሪዞርት ተካሄደ።
የመርሃ ግብሩ ዋና ዓላማ በስምጥ ሸለቆ ሐይቆችና በኦሞ–ጊቤ ተፋሰሶች በተደጋጋሚ የሚከሰቱ የጎርፍ አደጋዎችን ለመቀነስ የተዘጋጁ ጥናቶችንና የታቀዱ የጎርፍ አደጋ ቅነሳ ሥራዎችን በጋራ ለመገምገም ነው።
በወርክሾፑ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ፣ ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የዘርፉ ባለሙያዎች፣ ከውጭና ከሀገር ውስጥ የአዋጭነት ጥናት አቅራቢዎች፣ እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ጎርፍ መከላከል ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ተመስገን ከተማ፣ ፕሮጀክቱ እስካሁን ያከናወናቸውን ተግባራት በአጭር, በመካከለኛ በረጅም ጊዜ በተመለከተ ለተሳታፊዎች ዝርዝር ገለጻ አድርገዋል።
አቶ ተመስገን ወርክሾፑ በተፋሰሶቹ የሚከሰቱ የጎርፍ አደጋዎችን በዘላቂነት ለመቀነስ፣ ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ ማህበረሰቦችን ችግር ለመቅረፍና ተገቢ የጎርፍ መከላከል መፍትሔዎችን ለመለየት የተዘጋጁ ጥናቶችን በጋራ ለመገምገም ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።
በሁለቱ ቀናት የሚካሄደው ወርክሾፕ የፕሮጀክቱን ቀጣይ ሥራዎች ለማስፈጸም መሠረት የሚሆኑ የአዋጭነት ጥናቱንና ዝርዝር ዲዛይኑን በመገምገም የባለሙያዎችና የተሳታፊዎችን ግብዓት ለመሰብሰብ እንደሚያስችል ተመልክቷል።
ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto