የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ተወካይ ጋር ተወያዩ

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ተወካይ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11/2018 ዓ.ም. (ው.ሚ.ኢ)

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የኢትዮጵያና የአፍሪካ ህብረት ተወካይ ክብርት ኢንጅነር ለይላ ትራውሬ ጋር በውሃና ኢነርጂ ዘርፎች በሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ዙሪያ ተወያዩ።

ሚኒስትሩ በውሃ ዘርፍ የሚከናወኑ ሥራዎች ህብረተሰቡን በቀጥታ ተጠቃሚ እያደረጉ መሆናቸውን ገልፀው፣ በተለይም የአረንጓዴ አሻራ ሥራ ለአየር ንብረት ጥበቃ፣ ለውሃ ሀብት መጠን መጨመርና ለምግብ ዋስትና ያለውን ጠቀሜታ አጉልተዋል።

በኢነርጂ ዘርፍም የተመዘገቡ ውጤቶችን ጠቅሰው፣ ከህዝብ ቁጥርና ፍላጎት እድገት ጋር ተያይዞ የውሃና ኢነርጂ አቅርቦትን ለማስፋፋት ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ተጨማሪ የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ጠይቀዋል።

ክብርት ኢንጅነር ለይላ ትራውሬ በበኩላቸው ለተደረገላት መልካም አቀባበል ምስጋናዋ የላቀ መሆኑን ገልፃለች። አያይዛም ተወካዮ ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች እያሳየች ያለውን እድገት እንዲሁም በውሃና ኢነርጂ ዘርፎች የተከናወኑ ሥራዎችን አድንቀው፣ በቀጣይም የተጀመሩ የልማት ሥራዎች እንዲጠናከሩ ባንኩ የበኩሉን ድጋፍ እንዲደርግ የበኩሏን ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ገልፃለች። ፊስቡክ

https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/

ቴሌግራም

http://t.me/mowieethiopia

ዌብሳይት

http://mowe.gov.et

X/ትዊተር

https://x.com/mowe_ethiopia

ዩቱዩብ

https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s

ቲክቶክ

tiktok.com/@mowetikto

See

Share this Post