የውሃና ኢነርጂ ዘርፍ የሪፎርም አፈጻጸም ለኢንስፔክሽን ቡድን ቀረበ

የውሃና ኢነርጂ ዘርፍ የሪፎርም አፈጻጸም ለኢንስፔክሽን ቡድን ቀረበ

ነሐሴ 7/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ዘርፍ የአገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የዝግጅት ምዕራፍ አፈጻጸም ሪፖርት ለኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ቡድን ቀርቧል። በአቀራረቡም በተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች ላይ ግብዓትና ግብረመልስ ተሰጥቷል።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ በመድረኩ ሚኒስቴሩ በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ የተሻለ አገልግሎትና ተቋማዊ አቅም ለማረጋገጥ እያከናወናቸው ስላሉ የሪፎርም ሥራዎች ገለጻ ሰጥተዋል። በተለይም በሚኒስቴሩና በተጠሪ ተቋማት የተጀመሩ ቁልፍ የለውጥ ሥራዎችን አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የብቃት ሥራ አመራር ፕሮጀክት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊና የሱፐርቪዥን ቡድኑ አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ አጥሬ፣ ኢንስፔክሽኑ የሚኒስቴሩንና የተጠሪ ተቋማቱን አፈጻጸም በመገምገም የተገኙ ልምዶችንና የማሻሻያ አቅጣጫዎችን ለመለየት የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል።

የሚኒስቴሩ የሥራ አመራር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ኦልቀባ ባሼ በሪፖርቱ የተካተቱ የዝግጅት ምዕራፍ ሪፎርም ሥራዎችን አቅርበዋል። ሚኒስቴሩ በአገልግሎት ጥራት፣ በፈጣን ለውጥና በተቋማዊ አቅም ማሻሻያ ላይ ያተኮሩ ተግባራትን ማከናወኑም ተገልጿል።

በተጨማሪም የሚኒስቴሩ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ አቶ አለሙ መንገሻ የፖሊሲና የሕግ ማዕቀፎች፣ ስትራቴጂዎች፣ ማኑዋሎችና መመሪያዎች እንዲሁም የፋይናንስ አፈጻጸምና ሌሎች በሪፎርሙ የተከናወኑ ሥራዎችን በሰነድ በማስደገፍ በስፋት አቅርበው በጥልቀት ተገምግመዋል።በዚህም የተገኙ ጠንካራ ጎኖች፣ የሚሻሻሉ ጉዳዮችና ቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ይለያሉ።

የሪፖርት አቀራረቡን ተከትሎ ኢንስፔክሽን ቡድኑ በሚኒስቴሩና በተጠሪ ተቋማት የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎችን በሰነድና በመስክ ምልከታ ያረጋግጣል።

የኢንስፔክሽኑ ሂደት ሲጠናቀቅ የሚለዩ ግኝቶችና የማሻሻያ ሀሳቦች በግብረመልስ ሰነድ ይካተታሉ። ይህም በቀጣይ የሚከናወኑ የሪፎርም ሥራዎችን ለማጠናከርና የሚኒስቴሩን አገልግሎትና አስተዳደር ለማሻሻል ግብዓት ይሆናል።

ፌስቡክ

https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/

ቴሌግራም

http://t.me/mowieethiopia

ዌብሳይት

http://mowe.gov.et

X/ትዊተር

https://x.com/mowe_ethiopia

ዩቱዩብ

https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s

ቲክቶክ

tiktok.com/@mowetikto

Share this Post