ሚኒስቴሩ በሲዳማ ክልል ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ ባካሄደው የክረምት በጎ ተግባር ከማህበረሰቡ ምስጋና ተቸረው።
ሚኒስቴሩ በሲዳማ ክልል ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ ባካሄደው የክረምት በጎ ተግባር ከማህበረሰቡ ምስጋና ተቸረው።
ሀዋሳ፣ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም. (ው.ኢ.ሚ)
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሲዳማ ክልል ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ ዲላ አፍራራ ቀበሌ ባካሄደው የክረምት በጎ ተግባር መርሃ ግብር ለአካባቢው ማህበረሰብ ተጨባጭ ጥቅም የሚያስገኙ የተለያዩ ሥራዎችን በማከናወኑ ከአካባቢው ነዋሪዎች ከፍተኛ አድናቆትና ምስጋና ተችሮታል።
በመርሃ ግብሩ የ7 አቅመ ደካማ ዜጎች መኖሪያ ቤቶችን የመገንባት ሥራ በአፋጣኝ እንዲጀመር ተደርጓል። በተጨማሪም የአገራዊ አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ለማሳካት 5,000 ችግኞች ተተክለዋል።
እንዲሁም በደም እጥረት ምክንያት ሊያጋጥሙ የሚችሉ የሕይወት አደጋዎችን ለመቀነስ በማሰብ የሚኒስቴሩ አመራሮችና ሠራተኞች በበጎ ፈቃድ የደም ልገሳ አካሂደዋል።
በትምህርት ዘርፍም በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩ ለ500 ተማሪዎች ለ2019 የትምህርት ዘመን የሚያስፈልጉ የትምህርት ቁሳቁሶች፣ ማለትም ደብተር፣ እርሳስ፣ እስክርቢቶ፣ ላጲስ እና መቅረጫ በመለገስ ድጋፍ ተደርጓል።
በተጨማሪም ለአካባቢው ወጣቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የሕይወት ልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር በማካሄድ በሀገር ግንባታና በማህበረሰብ አገልግሎት ያላቸውን ሚና ለማጠናከር እንዲሁም የበጎ ፈቃድ ባህልን ለማጎልበት የግንዛቤ ሥራ ተከናውኗል።
በአካባቢው የሚኖሩት ወ/ሮ አበራሽ ታመነ፣ ወ/ሮ ሕይወት ጴጥሮስ እና አቶ ታደሰ አብርሃም እንደገለጹት ሚኒስቴሩ ለማህበረሰቡ እያደረገ ያለው በጎ አስተዋፅኦ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ መሆኑን በመግለጽ ለሚኒስቴሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በቀጣይም የመንግሥትን የማህበራዊ ኃላፊነት ፕሮግራሞች በማጠናከር ለማህበረሰቡ ዘላቂ ጥቅም የሚያስገኙ የበጎ ተግባራትን በስፋት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።
ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto