የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሲዳማ ክልል የክረምት የበጎ አድራጎት መርሃ ግብር አካሄደ
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሲዳማ ክልል የክረምት የበጎ አድራጎት መርሃ ግብር አካሄደ
ሲዳማ፣ ሸበዲኖ ወረዳ፣ ሀምሌ 30/2018 ዓ.ም. (ው.ኢ.ሚ.) – የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የክረምት ወቅት የበጎ አድራጎት መርሃ ግብርን በሲዳማ ክልል፣ በሸበዲኖ ወረዳ በማካሄድ ለማህበረሰቡ ተጨባጭ ድጋፍ አድርጓል።
መርሃ ግብሩ የአረንጓዴ ልማትን ከማስፋፋት ባሻገር ማህበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት የተጎዱና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ዜጎች ለማገዝ ያለመ ሲሆን፣ የሚኒስቴሩ አመራሮች፣ ሰራተኞች እና የአካባቢው አመራሮች በንቃት ተሳትፈዋል።
በመርሃ ግብሩ ወቅት ለ7 አባወራ ቤተሰቦች የመኖሪያ ቤቶቻቸው ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ ለመስራት ለኑሮ ምቹ እንዲሆኑ ለማድረግ ቅድመ ሁኔታ ተሠርቷል።
ይህም ለተጠቃሚ ቤተሰቦች የተሻለ የመኖሪያ ሁኔታ እንዲኖራቸው ያግዛል። በተጨማሪም ለአካባቢው ተማሪዎች 500 ደርዘን ደብተሮች ተሰጥተዋል። ድጋፉ የተደሰገላቸው ተማሪዎች በአዲሱ የትምህርት ዘመን በተሟላ የመማሪያ ግብዓት እንዲጀምሩ የሚያግዝ ሲሆን፣ የትምህርት ተሳትፎን ለማጠናከርም አስተዋጽኦ ያበረክታል። ከዚህ በተጨማሪ የደም ልገሳ መርሃ ግብር ተካሂዶ የሚኒስቴሩ አመራሮችና ሰራተኞች በበጎ ፈቃድ ደም በመለገስ ህይወትን ለማዳን ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል።
የደም ልገሳው በጤና ተቋማት ለሚገኙ የደም ፍላጎቶችን ለማሟላት እና የሰብአዊነት እሴትን ለማጠናከር የሚያገለግል ተግባር ነው። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እንዲህ ያሉ የበጎ አድራጎት ተግባራት የተቋሙን ማህበራዊ ኃላፊነት ከማሳየት ባለፈ የመንግስትና የህብረተሰብ ትስስርን ለማጠናከር፣ የመረዳዳት ባህልን ለማስፋፋት እና በዜጎች ህይወት ላይ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት በቀጣይነት እንደሚሰራ ገልጿል።
መርሃ ግብሩ የመንግስት ተቋማት ከዋና ተልዕኳቸው ጎን ለጎን ለማህበረሰብ የሚያበረክቱትን ማህበራዊ አስተዋፅኦ የሚያሳይ ተግባር ሲሆን፣ የመረዳዳት፣ የመተባበር እና የአብሮነት እሴቶች እንዲጠናከሩ አስፈላጊ ሚና ይጫወታል ሲሉ ገልፀዋል።