እየተከልን ያለነው ችግኝ ብቻ ሳይሆን የምግብ ሉዓላዊነታችንን ለማረጋገጥ ጭምር ነው።
እየተከልን ያለነው ችግኝ ብቻ ሳይሆን የምግብ ሉዓላዊነታችንን ለማረጋገጥ ጭምር ነው።
ሀዋሳ ሐምሌ 30/2018ዓ.ም(ው.ኢ.ሚ)
የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች የአረንጓዴ አሻራና የበጎ አድራጎት መርሀ ግብርን በሲዳማ ብሄራዊ ክልል ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን በሸበዲኖ ወረዳ በአንፈራራ ቀበሌ ባካሄደበት ወቅት እየተከልን ያለነው ችግኝ ብቻ ሳይሆን የምግብ ሉዓላዊነታችንን ጭምር መሆኑ ተገለጸ ።
በፕሮግራሙ ላይ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በክልሉ የሚከናወነው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብርም የአካባቢ መራቆትና የአፈር መሸርሸርን በመቀነስ፣ የውሃ ምንጮችን በማጎልበት ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ያስችላል ብለዋል።
በመሆኑም በወረዳዋ ከአካባቢው አየር ንብረት ጋር ተስማሚ የሆኑና የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጡ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን በዚሁ አካባቢ በወረዳ አመራሩ የተለዩ 500 ተማሪዎች የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች ድጋፍ ያደረግን ሲሆን በቀጣይነት ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል ።
በተመሳሳይ በዚሁ ወረዳ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሰባት አባዎራዎች በተወሰነው ደረጃ መሠረት የአቅመደካሞችን ቤት ግንባታ ወደ ተግባር እንደሚገባ ተናግረዋል።
ከዚህ ጎን ለጎን ክቡር ሚኒስትሩ ፣የክልሉ ተወላጅ ክቡር ዶ/ር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ እና ሌሎች አመራሮች ልምድ እና ተሞክሯቸውን በማካፈል ወጣቶችን የማነቃቃት ተግባር ተከናውኗል፡፡
የሲዳማ ክልል ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፃዲቁ በጢሶ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በዞኑ በተለያዩ ወረዳወች ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸው በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርም በተመረጡ ቀበሌዎች ከ50 ሺ በላይ ችግኞች መትከል ፤ ሰባት ለሚሆኑ አቅመ ደካማ ወገኖቻችን የመኖሪያ ቤት ማስጀመሪያ ፕሮግራም ማከናወን፤ 500 ለሚሆኑ ደጋፊ ለሌላቸው ተማሪዎች የት/ርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግና የደም ልገሳ መርሀግብር ማከናወኑን ገልጸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
በመርሀ ግብሩ ላይ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ፣ አማካሪዎች ፣የወረዳው ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት መሪዎች እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ ተሳትፈዋል።
ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto