የስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ተፋሰስ ቤዚን ፕላን ክለሳ ላይ የባለሙያዎች ስልጠና ተሠጠ

የስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ተፋሰስ ቤዚን ፕላን ክለሳ ላይ የባለሙያዎች ስልጠና ተሠጠ

ሀምሌ 29/2018 ዓ.ም. ሀዋሳ (ው.ኢ.ሚ.) – የስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ተፋሰስ የሁኔታ ዳሰሳ፣ የቤዚን ፕላን ዝግጅትና ክለሳ ላይ ያተኮረ የባለሙያዎች ስልጠና በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና በWLRC BRIGHT Project በጋራ በተዘጋጀ የበጀት ድጋፍ በሀዋሳ ተካሂዷል።

ስልጠናው የተፋሰሱን ወቅታዊ ሁኔታ በመዳሰስ የቤዚን ፕላኑን ለማዘመን፣ ለመከለስና ለተግባራዊ አፈጻጸም የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ለማጠናከር ያለመ ሲሆን፣ ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ ከአራቱ ክልሎች፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ከውሃና መሬት ሀብት ማዕከል እና ከተፋሰሱ ባለድርሻ ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

በስልጠናው የቤዚን ፕላኑ የአሁኑ ደረጃ፣ የክለሳ ሂደት፣ የተለዩ ክፍተቶች እና የቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች በባለሙያዎች እየቀረቡ ሲሆን፣ የተፋሰሱን ሀብቶች በተቀናጀ መንገድ ለማስተዳደር የቤዚን ፕላኑን ወቅታዊና ተግባራዊ ለማድረግ የሚያግዝ መሆኑ ተገልፆል።

Share this Post