ክቡር ዶ/ር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ ከእስራኤል አምባሳደር ጋር በቴክኖሎጂ ሽግግርና በውሃና ኢነርጂ ትብብር ላይ ተወያዩ።
ክቡር ዶ/ር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ ከእስራኤል አምባሳደር ጋር በቴክኖሎጂ ሽግግርና በውሃና ኢነርጂ ትብብር ላይ ተወያዩ።
አዲስ አበባ : ሀምሌ 27/2018ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ)
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ክቡር ዶ/ር አቨራሃም ንጉሴን ተቀብለው በውሃ፣ በኢነርጂና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱ ኢትዮጵያ በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ እያካሄደች ያለውን የሪፎርምና የዘመናዊ አሰራር ጉዞ ለማፋጠን የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የልምድ ልውውጥ፣ የባለሙያዎች አቅም ግንባታ እና የጋራ ፕሮጀክቶች ማስፈጸም ቅድሚያ የሚሰጣቸው የትብብር መስኮች መሆናቸውን በስፋት አንስተዋል።
በተለይም በውሃ ሀብት አስተዳደር፣ በውሃ ጥራት ምርመራ፣ በውሃ ማጣሪያ ቴክኖሎጂ፣ በሶላር ኢነርጂ፣ በዲጂታል የውሃ መረጃ ሥርዓቶችና በዘመናዊ የመለኪያ መሣሪያዎች ላይ ያለውን ትብብር ለማስፋፋት ሁለቱም ወገኖች ተስማምተዋል።
ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto