የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች አረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር አከናወኑ።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች አረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር አከናወኑ።
አደአ ሐምሌ 27፣ 2018 (ውኢሚ)
በምስራቅ ሸዋ ዞን አደአ ወረዳ በመገኘት በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮንች ግኞች ተስፋን እንትከል በሚል መሪ ቃል አሻራቸውን አስቀምጠዋል።
በመርሀ ግብሩ የተገኙት ሚኒስትሩ እንዳሉት፥ ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ ዐሻራ የተተከሉ ችግኞች ተጨባጭ ለውጦችን እያመጡ ነው ብለዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ በማከል በወረዳዋ ከውሃና መሬት ሀብት አስተዳደር ጋር በጋራ የአፈር መሸርሸርን በመቀነስ፣ የአፈር ለምነትን በመጠበቅና የተፋሰስ ሥነ ምህዳርን በማጠናከር ስማርት ቪሌጅ እየተገነባ እንደሆነ ገልጸዋል ።
በዚህም ከአካባቢው አቀማመጥ ጋር ተያይዞ የመሬት መሸርሸር አደጋን ከመከላከል ባሻገር ውሃ ወደ ከርሰ ምድር እንዲሰርግ በማድረግ የተፈጥሮ ምንጮች፣ ጉድጓዶችና ወንዞች የውሀ መጠን እንዲጨምር እያገዘ ነው ብለዋል።
በተጨማሪም አረንጓዴ ዐሻራ የተፋሰስ ጥበቃን በማጠናከር የግድቦችን ደኅንነትና የውሃ ምንጮች እየጠበቀ ይገኛል ብለዋል ።
ክቡር ሚኒስትሩ የአካባቢው ማህበረሰብ የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ አደራ ብለዋል።
በእለቱ በወረዳዋ ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች የመማሪያ መሳሪያ ድጋፍ ተደርጓል ።
በመርሀ ግብሩ ላይ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች እና ሰራተኞች የካባቢው ማህበረሰብ በጋራ አሻራቸውን አስቀምጠዋል ።
ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto