ስምንት ዓመታት፤ ቀጣይነት ባለው ተግባር!
ስምንት ዓመታት፤ ቀጣይነት ባለው ተግባር!
ቢሾፍቱ ሐምሌ 27/2018ዓም(ው.ኢ.ሚ)
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር በሕዝባዊ
ቁርጠኝነትና ኢትዮጵያውያን በጋራ በመቆም አረንጓዴ፣ ዘላቂ እና ለቀጣዩ ትውልድ የሚበጅ ነገን መገንባት ይቻላል በሚለው የጋራ እሳቤ ከተጀመረ ስምንት ዓመታትን በማስቆጠር ዛሬም በተጠናከረ መልኩ ቀጥሏል።
ዛሬ ኢትዮጵያውያን ለቀጣዩ ትውልድ የሚተርፍ ዘላቂ ዐሻራ ለማሳረፍ በጋራ የሚሰባሰቡበት ዓመታዊው የአንድ ጀምበር ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ነው።
በዚሁ መሰረት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ በምስራቅ ሸዋ ዞን አደአ ወረዳ ጎዲኖ ቀበሌ በ"ጎዋ ወርኮ" በተባለ ስፍራ "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር እያከናወኑ ሲሆን፣ 11,000 ችግኞች ከአካባቢው ማኅበረሰብ፣ ከአመራሮች፣ ከሠራተኞችና ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመሆን በባህላዊ ዘፈንና በደማቅ መንፈስ እየተተከሉ ይገኛሉ።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር የደን ሽፋንን ከማሳደግ ባሻገር የውሃ ምንጮችን በመጠበቅ፣ የአፈር መሸርሸርን በመቀነስ፣ የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋምና የሕዝቡን የኑሮ መሰረት በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ ያለው ሀገራዊ ንቅናቄ ሆኗል።
በተለይም ለውሃና ኢነርጂ ዘርፍ የደን ልማት የውሃ ተፋሰሶችን በመጠበቅ፣ የግድቦችን ደለል በመቀነስ፣ የመስኖና የመጠጥ ውሃ ምንጮችን በማጠናከር እንዲሁም የሀገራችንን የኃይል ልማት በዘላቂነት ለመደገፍ የጎላ አስተዋፅኦ ያበረክታል።
የዛሬው የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብርም ከችግኝ ተከላ ባሻገር የአካባቢ ጥበቃ፣ የሕዝብ ተሳትፎ፣ የተቋማት ትብብርና የትውልድ ኃላፊነትን የሚያጠናክር ተግባር መሆኑን አንጸባርቋል።
"ተስፋን እንትከል" የሚለውን መሪ ቃል በተግባር በማሳየት የዛሬው ተሳትፎ ለአረንጓዴ፣ ለበለፀገችና ለዘላቂ ኢትዮጵያ የሚተርፍ ዐሻራ የሚያኖር እንደሆነ ተሳታፊዎች ገልፅዋል።
ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto