የደናክል ቤዚን ፕላን ዝግጅት መነሻ ሪፖርት ቀርቦ ግምገማ ተካሄደ።

የደናክል ቤዚን ፕላን ዝግጅት መነሻ ሪፖርት ቀርቦ ግምገማ ተካሄደ።

ሐምሌ 21/2018 ዓ.ም. (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የደናክል ቤዚን ፕላን ዝግጅት መነሻ ሪፖርት ቀርቦ በተመረጡ የኮሚቴ አባላት እና ባለሙያዎች ግምገማ ተካሂዶበታል።

ሰመራ፣ወልዲያና መቀሌ ዩኒቨርሲቲ በትብብር ባዘጋጁት ቤዚን ፕላን ላይ ተመርኩዞ የቀረበው የመነሻ ሪፖርት በቀጣይ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት የተሰጡ አስተያየቶች እንዲካተቱበት ይደረጋል።

የደናክል ቤዚን ፕላን ዝግጅት ትግበራ ከአውሮፓ ህብረት ተቋም በሚደረግ የፋይናንስና ቴክኒካል ድጋፍና ከቤዚን አቀፍ ዘላቂ ማረጋገጫ (BaSERNET) ፕሮጀክት ጋር በትብብር እየተከናወነ ይገኛል።

ኢትዮጵያ ካሏት 12 ተፋሰሶች መካከል 9ኙ የቤዚን ፕላን የተዘጋጀላቸው ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የደናክልና የተከዜ ቤዚኖች ፕላን በዝግጅት ላይ ይገኛሉ።

የቤዚን ፕላኑ ሲጠናቀቅ በደናክል ተፋሰስ የውሃ ሀብትን በተቀናጀ መንገድ ለማልማትና ለማስተዳደር፣ የውሃ አጠቃቀምን ለማሻሻል፣ የአካባቢ ጥበቃን ለማጠናከር እንዲሁም የውሃ ልማት ፕሮጀክቶችን በቅድሚያ ለመለየትና በተቀናጀ መልኩ ለመተግበር እንደ መመሪያ ሰነድ ያገለግላል።

እንዲሁም የአካባቢውን ዘላቂ ልማት ከማፋጠን ባሻገር ለማህበረሰቡ የውሃ ተጠቃሚነትን እና የኢኮኖሚ እድገትን ለማጠናከር አስተዋጽኦ ያበረክታል።

Share this Post