በአደሌ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና በልማት ባንክ በኩል እየተከናወኑ ያሉት የኤሌትሪፊኬሽን ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ተገመገመ፡፡

በአደሌ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና በልማት ባንክ በኩል እየተከናወኑ ያሉት የኤሌትሪፊኬሽን ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ተገመገመ፡፡

ሰኔ4/2018 ዓም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በአደሌ ፕሮጀክት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና በልማት ባንክ በኩል እየተከናወኑ ያሉት የኤሌትሪፊኬሽን ፕሮጀክቶች አፈጻጸምን ገምግሟል።

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ በመጀመርያ የገመገሙት በአደሌ ፕሮጀክት በአዲስ አበባ እና በሌሎች የክልል ከተሞች ማለት አምቦ፣ ነቀምት፣ አሶሳ፣ ቢሾፍቱ፣ ሱልልታ እና ደብረብሃን እየተከናውነ ያሉት የኔትዎርክ ማሻሽያና ማጠናከርያ ስራዎችን እና በዝግጅት ምዕራፍ ባሉት ጂጅጋ፣ ሆሳእና፣ ዲላ እና አሰላ የገመገሙ ሲሆን በከተሞች ካለው የኢነርጂ ፍላጎት እድገት አንጻር ቀድመን ማስተካከል ያለብን የኤሌትሪፊኬሽን መሰረተ ልማት ዋና ተግባር መሆኑ በመገንዘብ ፕሮጅክቱ ቶሎ ብሎ የሚጠናቀቁበት እቅድ ታቅዶ ስራዎችን የሚፋጠኑበት አግባብ እንዲኖር አሳስበዋል።

በተመሳሳይ የሶላር ሚኒ ግሪድ ፕሮጀችት የተገመገመ ሲሆን በዚህ ፕሮጀት በጠቅላላ 99 ሶላር ሚኒ ግሪዶችን የሚገነቡ ሲሆን እስከአሁን 22 ሚኒ ግሪዶች ተጠናቅቀው አግልግሎት መስጠት የጀመሩ ሲሆኑ ቀሪዎችን በተለያዩ ደረጃ ያሉት መሆናቸው ሲጠቀስ ክቡር ሚኒስትሩ ፕሮጀክቱ አፈጻጸሙ እየተሻሻለ መሆኑ በመጥቀስ በተለይ የኃይል ማመንጫቸው ተጠናቆ የስርጭት ስራ በመጠባበቅ ያሉት አስፈላጊ የመስክ ክትትል በማድረግ ህብረተሰቡ የኤሌትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ በማሳሰብ በተለይ ደግሞ ልዩ ትኩረት የሚያስፈልጋቸው አከባቢዎችን የሚኒስቴር መስሪያቤቱ እና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የበላይ አመራሮች የመስክ ክትትል እንዲደረግ አቅጣጫ ተስጥቶባቸዋል።

ባጠቃላይ በልማት ባንክ በኩል ለገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ያለው የፋይናንስ አቅርቦት ፕሮጀክት ሲሆን፣ ይህ ፕሮጅክት ከግሉ የሶላር እና የፋይናንስ ዘርፍ የሚተገበር በመሆኑ እና የገጠር ማህበረሰብ በማይክሮ ፋይናንስ በኩል የብድር አቅርቦት የሚያመቻች በመሆኑ ለሶላር ስርጭት ከፍተኛ አስትዋጻኦ ያለው መሆኑን በመጥቀስ ልማት ባንክ ይህ የፋይናንስ አቅርቦት ለሁሉም ማህበረሰብ ተደራሽነት የሚሆንበት አሰራር እንዲያመቻች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስፈላጊ ድጋፍ የሚያድረግ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በመጨረሻ አጠቃላይ የፕሮጀክቱ የፊዚካል እና የፋይናንስ አፈጻጸም ሲታይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መሆኑ በመጥቀስ ከዚህ በላይ አፈጻጸም የሚጠበቅ በመሆኑ እስከሚቀጥለው አንድ አመት ባለው ጊዜ ውስጥ ፕሮጀክቶቹ እንዲጠናቀቁ አሳስበዋል።

በግምገማው ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና ከልማት ባንክ የሚመለከታቸው ኃላፊኢዎች እና የፕሮጀቱ አስተባባሪዎችን በውይይቱ ላይ ተሳትፈዋል።

Share this Post