የባዘሪኔት ፕሮጀክትን ዲጂታላይዝ ለማድረግ በሚያስችሉ የኮቦቱልቦክስ እና ፓወር ቢአይ ሶፍት ዌር ላይ ስልጠና እየተሠጠ ነው።
የባዘሪኔት ፕሮጀክትን ዲጂታላይዝ ለማድረግ በሚያስችሉ የኮቦቱልቦክስ እና ፓወር ቢአይ ሶፍት ዌር ላይ ስልጠና እየተሠጠ ነው።
አዳማ ግንቦት 26/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ)በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር
በባዘሪኔት (BaSRINET) ፕሮጀክት ውስጥ ቀልጣፋ የመረጃ ማሰባሰብ፣ ትንተና እና ሪፖርት አቀራረብን ለማጠናከር ያለመ የኮቦቱልቦክስ (KoboToolbox) እና ማይክሮሶፍት ፓወር ቢአይ (Microsoft Power BI) ስልጠና እየተሰጠ ነው ።
በቦታው ተገኝተው የስልጠናውን መርሃ ግብሩ ያስጀመሩት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የቤዚን ፕላን ዴስክ ኃላፊ አቶ አሰግድ አጀመ ስልጠናው የተቀናጀ ውሃ ሀብት አስተዳደር ስር ባለው የባዘር ኔት ፕሮጀክት መዘጋጀቱን ገልጸው በኮቦ ቱል ቦክስ እና ማይክሮሶፍት ፓወር ቢአይ ላይ ያለብንን ክፍተት ለመሙላት ታሳቢ ያደረገ ሲሆን ሰልጣኞች ለፕሮጀክትም ሆነ መደበኛ ስራን ለማፋጠን እንዲችሉ የተዘጋጀ አቅም ግንባታ ስልጠና ነው ብለዋል።
አቶ አሰግድ አክለውም ስልጠናው በተለይ መረጃዎችን በተገቢው መንገድ ሰብስበን ለተገልጋይ ምቹ ከማድረግ አንጻር ያለብንን ክፍተት ለመሙላት እንዲያስችል ብሎም የዲጅታል አሰራርን ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚረዳ ገልጸዋል።
ሰልጣኞች ስልጠናውን የሚወስዱት የተቋማችንን ነባራዊ ሁኔታ በሚያውቁ አሰልጣኞች በመሆኑ እንደ ጥሩ አጋጣሚ ወስዳችሁ በትኩረት በመሠልጠን ወርዳችሁ ተግባራዊ ማድረግ እንድትችሉ በነቃ ሁኔታ እንድትከታተሉ አደራ በማለት ስልጠናውን አስጀምረዋል።
ለስልጠናው ተሳታፊዎች መልዕክት ያስተላለፋት የባዘርኔት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሞላ ረዳ በባዘሪኔት (BaSRINET) ፕሮጀክት ውስጥ ቀልጣፋ የመረጃ ማሰባሰብ፣ ትንተና እና ሪፖርት አቀራረብን ለማጠናከር ያለመ የኮቦቱልቦክስ (KoboToolbox) እና ማይክሮሶፍት ፓወር ቢአይ (Microsoft Power BI) ስልጠና አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ ስራ እንደሚረዳ ገልጸዋል።
ስልጠናው በአቶ ሀብታሙ እና በአቶ ስንታየሁ አስተባባሪነት የኮቦቱልቦክስ እና የማይክሮሶፍት ፓወር ቢአይ መሠረታዊ ፅንሰ-ሀሳቦች ለፕሮጀክቱ ስኬት ስላላቸው ሚና ሰፊ ገለጻ ተሰጥቷል።
ስልጠናዎች ላይ ትኩረት የተደረገው በዲጂታል መረጃ አሰባሰብ፣ ትንተና እና በቪዥዋላይዜሽን (Data Visualization) ዙሪያ ሲሆን የኮቦ ቱልቦክስ እና ሞባይል መረጃ አሰባሰብ በኮቦ ቱልቦክስ (KoboToolbox) እና በኦዲኬ (ODK) መተግበሪያዎች ላይ እንደሚያተኩር ፣ ሰልጣኞች የቅፅ ዝግጅት፣ የመረጃ አሰባሰብ፣ የመረጃ አስተዳደር እና የሪፖርት አቀራረብ መሰረታዊ ክህሎቶችን በተግባር ልምምድ እንዲያደርጉ እንደሚረዳ አሰልጣኙ ገልጸዋል።
ስልጠናው ፎርሞችን ማሰማራትና መረጃ መሰብሰብ የባዘሪኔት(BaSRINET)ፕሮጀክት መረጃ አሰባሰቡ በቀጥታ ከባዘሪኔት (የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር - IWRM) ፕሮጀክት ዓላማዎችና መለኪያዎች ጋር በተያያዘ መልኩ እንዲከናወን ያደርጋል፣የመረጃ ትንተና እና ኤክስፖርት የተሰበሰቡ መረጃዎችን በExcel፣ CSV እና በሌሎች ቅርፀቶች በመቀየር ለቀጣይ ስራ እንዴት ማዘጋጀት እንደሚጠቅም በስልጠናው ላይ በተግባር ታይቷል።
ይህ ስልጠና በአቶ ሀብታሙ እና በአቶ ስንታየሁ ዋና አሰልጣኝነት እንዲሁም በሌሎች አሰልጣኞች ረዳትነት እየተመራ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ ቀናት በተለያዩ ቴክኒካዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚቀጥል ታውቋል።
በስልጠናው ላይ የቤዚን አስተዳደር ሀላፊዎች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።