የኢነርጂ ረቂቅ ፖሊሲ ጸደቀ

የኢነርጂ ረቂቅ ፖሊሲ ጸደቀ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 55ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ 13 ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ምክር ቤቱ ከተወያየባቸው ጉዳዮች መካከል የኢነርጂ ረቂቅ ፖሊሲ አንዱ ነው፡፡

ፖሊሲው ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም፣ ከአሥር አመቱ የልማት ዕቅድ፣ ከአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ስትራቴጂ፣ ከምዕተ አመቱ የልማት ግቦች እና ከሌሎች ፖሊሲዎች ጋር የተጣጣመ መሆኑ ተገልጿል።

በመሆኑም የአገራችንን የኢነርጂ ሀብት በአነስተኛ ዋጋ በማልማት ዘላቂ፣ አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ በዋጋ ተመጣጣኝና ተወዳዳሪ የኢነርጂ አቅርቦት እንዲኖርና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲያስችል ረቂቁ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱም በፖሊሲው ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብአቶችን በማከል በምክር ቤቱ ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ አመልክቷል፡፡

Share this Post