የተቀናጀና ዘላቂ የመሠረተ ልማት እና ሀብት ቁጠባ በመደመር እሳቤ!

የተቀናጀና ዘላቂ የመሠረተ ልማት እና ሀብት ቁጠባ በመደመር እሳቤ!

ግንቦት 13/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በለውጡ መንግስት በመደመር እሳቤ የአንድን ሀገር የኢኮኖሚ ጥንካሬና የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል በከተማም ሆነ በገጠር የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎችን የኤሌክትሪክ ኃይልና የንፁህ መጠጥ ውኃ ተደራሽነት ማረጋገጥ እጅግ ወሳኝነት አለው።

ሆኖም እነዚህን መሠረታዊ አገልግሎቶች በተናጠልና ባልተቀናጀ መልኩ መገንባት ከፍተኛ የሀብት ብክነትን፣ የጊዜ መጓተትንና የአሠራር መደራረብን ሲያስከትል መቆየቱ ይታወቃል።

በአሁኑ ወቅት ይህንን ክፍተት ለመሙላት የመጣው የተቀናጀ መሠረተ ልማት (Integrated Infrastructure) አቀራረብ እንደውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሶስቱን ወሳኝ ዘርፎች በአንድ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ በማስተሳሰርና አነስተኛ ሀብትን በመጠቀም ከፍተኛ የልማት ውጤት ለማምጣት በትኩረት ሲሰራ ቆይቷል።

ሀገራዊው የመሰረተ ልማት ስራዎች አንዱን ከሌላው ዘርፍ ጋር በማስተሳሰር ዜጎችን ይበልጥ ተጠቃሚ የማድረግ ዓላማ ያለው በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶታል።

በተለይም ቁልፍ የሆኑት የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን እና የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መስመሮች እርስ በርስ እንዳይጣረሱ እና ዘላቂ አገልግሎት እንዲሠጡ አቀናጅቶ መተግበርም አሁን ላይ ለሚታዩ ለውጦች ማሳያ ሆኗል።

የኮሪደር ልማት የከተሞችን ፈጣን ዕድገት በሚመጥን፣ የህብረተሰቡን የመሠረተ ልማት ጥያቄውን በሚመልስ እና ዘመናዊ የኑሮ ዘይቤ በማሟላት ረገድ ውጤታማ በመሆኑ፤ መሰረተ ልማቶችን አቀናጅቶ ለመምራት የሚያስችል ሰፊ ዕድል መፍጠሩን ባለፉት የለውጥ ዓመታት በተከናወኑ የመሰረተ ልማት ስራዎች ማየት ችለናል።

የተቀናጀ መሰረተ ልማት የኢኮኖሚ ዕድገት የማነቃቃት፣ ማህበራዊ አገልግሎት ተደራሽነት እና ፍትሐዊነት ማረጋገጥ እንዲሁም ለኑሮ ምቹና ተመራጭ ከባቢ ለመፍጠር የሚያስችል በመሆኑ ከፍተኛ ትኩረት አግኝቶ እየተተገበረ ይገኛል።

በከተሞች የተጀመረው የተሟላ የልማት ሥራ ተቀናጅቶ መተግበሩ በአጭር ጊዜ ለዜጎች የመሰረተ ልማት ጥያቄ ምላሽ ከመስጠቱም በላይ ቀደም ሲል በተበታተነ መንገድ ይካሄድ የነበረው የመሰረተ ልማት ግንባታ ያጋጥሙት የነበረውን ውስብስብ ችግሮች ለመፍታት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው።

የተቀናጀ መሰረተ ልማት ሁሉንም ዘርፎች ለማነቃቃት፣ ተቋማትን በአቅም እና በዕውቀት ለመገንባት፣ አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን እና ለማቀላጠፍ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር በመሆኑ የጎላ ጠቀሜታ አለው።

በመደመር እሳቤ ወደ ተግባር የገባው የተቀናጀ መሰረተ ልማት በውሃ፣ በኤሌክትሪክ ኃይል እና በሌሎቾ ዘርፎች የዜጎችን እርካታ ከማሳደጉም በላይ በሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ላይ የድርሻውን እየተወጣ ይገኛል።

ዛሬም በከተሞች ጥራት እና ፍጥነት በመጨመር የተለያዩ የመሠረተ ልማት ሥራዎች በተቀናጀ መልኩ እየተተገበሩ ሲሆን፤ በቀጣይ አምስት ዓመታት ይህንን የተቀናጀ አሰራር አጠናክሮ በማስቀጠል የዜጎችን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ይሰራል።

Share this Post