የዘፊኔ ከተማን የንፁህ መጠጥ ውሃ ና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት የህብረተሰቡን ችግር በዘላቂነት እንደሚፈታ ተገለጸ።

የዘፊኔ ከተማን የንፁህ መጠጥ ውሃ ና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት የህብረተሰቡን ችግር በዘላቂነት እንደሚፈታ ተገለጸ። ግንቦት 4/2018 ዓ.ም​(ው.ኢ.ሚ) ዘፊኔ፣ ጋሞ ዞን በጋሞ ዞን የዘፊኔ ከተማ ከ157 ሚሊዮንብር በላይ ወጪ የተገነባው ንፁህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት የህብረተሰቡን ችግር በዘላቂነት እንደሚፈታ ተገለጸ። በእለቱ በክልሉ ከመጠጥ ውሃ በተጨመሪ መካከኛ ሆስፒታልኝ ጨምሮ ሌሎች የልማት ስራዎችን ያስጀመሩት የክልሉ ርእሰ መስተዳድር የተከበሩ አቶ ጥላሁን ከበደ ህብረተሰቡ ይህ ተደራራቢ ልማት እንደሚገባው ገልጸው መንግስት ቃልን በተግባር የሚያሳይ ህዝባዊ ፓርቲ መሆኑን ገልጸዋል። የውሃ ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋም ፕሮጀክቱ የዘፍኔ ከተማ በቺላሼ ቀበሌ የሚኖሩ ከ34,118 በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገልጸው ለከተማው ነዋሪዎች አስተማማኝና ዘላቂ የውሃ አቅርቦት ከመስጠቱም በላይ በተለይ ውሃ ፍለጋ ረጅም ርቀት የሚጓዙ ሴቶችንና ህፃናትን የጊዜና የጉልበት ብክነት የሚያስቀር ከመሆኑም ባለፈ የውሃ ወለድ በሽታዎችን በመቀነስ የህዝብ ጤናን ለማሻሻልና ለከተማዋ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥርም ገልጸዋል። ​ፕሮጀክቱ በሰከንድ 27 ሊትር ውሃ የማመንጨት አቅም ያላቸው ሁለት ሪዘርቫየር ያለውና የኤሌክትሮ-ሜካኒካል ስራዎችም ተሰሰሩ ሲሆን በተጨማሪም የቆየው የ100 ሜ³ ማጠራቀሚያ ገንዳ የጥገና ስራ ተሰርቷል። ​የቧንቧ ዝርጋታው በአጠቃላይ 23.28 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የቧንቧ ዝርጋታ የተከናወነ ሲሆን፣ ይህም የማስተላለፊያና የስርጭት መስመሮችን ያካትታል። ፕሮጀክቱ ለውሃ አገልግሎቱ ​ 8 ክፍሎች ያሉት የአስተዳደር ቢሮ ህንፃ፣ የጥበቃ ቤቶች፣ የህዝብ መጸዳጃ ቤቶች እና የቆሻሻ ማጠራቀሚያን (Septic tank)ያካትታል። ​በአሁኑ ወቅት አዳዲስ የህዝብ ውሃ መጠጫ ቦኖዎችን የመገንባትና የነባሮችን የመጠገን ስራ የተከናወነ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ በተቀመጠለት የጥራት ደረጃና የጊዜ ገደብ ተጠናቆ ለአገልግሎት መብቃቱን ከወጣው መረጃ ለመረዳት ተችሏል። ፕሮጀክቱ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ውሃ ልማት ፈንድ ባስኬት ​ፕሮጀክት ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የውሃና ኢነርጂ ቢሮ በሚከታተለውና "ሚልኪ ኮንሰልቲንግ" በአማካሪነት እንዲሁም "ታሪኩ ገ/መስቀል GWWC" እና "ቤልት ጄኔራል ቢዝነስ" በሽርክና (J.V) በኮንትራክተርነት የተተገበረ ነው ። በምርቃት ፕሮግራሙ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር የተከናውኗል። በመርሀ ግብሩ የክልሉን ርእሰ መስተዳድርን ጨምሮ የክልልና የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች ና ባለሙያዎች የሀገር ሽማግሌዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

Share this Post