ለበሻሻ ከተማ የመጠጥ ውሃ ግንባታ ፣ የኤሌክትሮሜካኒካል አቅርቦትና ተከላ ፕሮጀክት የውል ስምምነት ተፈረመ።

ለበሻሻ ከተማ የመጠጥ ውሃ ግንባታ ፣ የኤሌክትሮሜካኒካል አቅርቦትና ተከላ ፕሮጀክት የውል ስምምነት ተፈረመ። ሚያዚያ 8/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በኦሮሚያ ክልል ጂማ ዞን ለምትገኘው የበሻሻ ከተማ የመጠጥ ውሃ ግንባታ፣ የኤሌክትሮሜካኒካል አቅርቦትና ተከላ ፕሮጀክት የውል ስምምነት ተፈረመ። የውል ስምምነቱን የፈረሙት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ክቡር ዶ/ር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ ሲሆኑ ውል የገባው ኮንትራክተር ሃቢብ ሁሴን የግንባታና የውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ነው። በውል ፊርማ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ለፕሮጀክቱ የተመደበው ጠቅላላ በጀት 591,181,588.38 ETB መሆኑን ገልጸው ወጪው በአፍሪካ የውሃ ፋሲሊቲ ፋይናንስ የሚደረግና በአፍሪካ ልማት ባንክ የሚሸፈን መሆኑን ተገልፀዋል። ፕሮጀክቱ በውሉ መሰረት በ18ወራት የሚጠናቀቅ ይሆናልም ተብሏል። የበሻሻ ከተማ የህዝብ ብዛት እ.ኤ.አ በ2022 18,890 ሲሆን በ2040 ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ተጠቃሚ ይሆናል ተብሎ ታሳቢ የሚደረገው የማህበረሰብ ቁጥርም 32,970 እንደሚሆን ተመልክቷል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከኮንትራክተሩ ጋር ከዚህ ቀደምም በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ በሚሰሩ ስራዎች ሲሰሩ የቆዩ መሆናቸውን ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ የጠቆሙ ሲሆን በጊዜው በነበረው ቆይታ ስራዎችን በጊዜና በጥራት ማጠናቀቃቸውን አስታውሰው አሁንም ይህንኑ አጠናክረው ማጠናቀቅ እንዳለባቸው በአፅንኦት አሳስበዋል።

Share this Post