ከአዩን የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የቧንቧ አቅርቦት ስራና ከጉራድ ሃሞሌ የኤሌክትሮሜካኒካል ዕቃ አቅርቦትና ተከላ ጋር የውል ስምምነት ተፈረመ።

ከአዩን የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የቧንቧ አቅርቦት ስራና ከጉራድ ሃሞሌ የኤሌክትሮሜካኒካል ዕቃ አቅርቦትና ተከላ ጋር የውል ስምምነት ተፈረመ። ሚያዚያ 1/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከአዩን የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የቧንቧ አቅርቦት ስራና ከጉራድ ሃሞሌ የኤሌክትሮሜካኒካል ዕቃ አቅርቦትና ተከላ ጋር በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ አማካኝነት ውል ስምምነት ተፈርሟል። የአዩን የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የቧንቧ አቅርቦት አቅራቢ ሹምቡሮ የፕላስቲክ ፋብሪካ ሲሆን አማካሪው ደግሞ የሶማሊ ጥናትና ዲዛይን ኢንተርፕራይዝ ነው። ለፕሮጀክቱ የተመደበው በጀት 200,624,244.55 የኢትዮጵያ ብር መሆኑ ተመልክቷል። ፕሮጀክቱ በሶማሌ ክልል ኖጎብ ዞን የሚተገበር ሲሆን በውሉ መሰረት በ90ቀናት የሚጠናቀቅ ይሆናል። ከጉራድ ሃሞሌ የኤሌክትሮሜካኒካል ዕቃ አቅርቦትና ተከላ በኩል የተፈረመው የውል ስምምነት ደግሞ ኮንትራክተሩ ኢሙ ጠቅላላ አስመጪ ኃላ የተ.የግል ኩባንያ ሲሆን የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፓሬሽን የሚያማክረው ነው። ለኮንትራቱ የተቀመጠው ወጪም USD 381,180.28 እና ETB 60,939,230.80 ሲሆን በአጠቃላይ የተመደበው በጀት በብር 120 ሚሊዮን በላይ ነው። ፕሮጀክቱ በሶማሊ ክልል ሊበን ዞን የሚተገበር ሲሆን በውሉ መሰረት በ150ቀናት የሚጠናቀቅ ይሆናል። ፕሮግራሞቹ በዋን ዋሽ ብሄራዊ ፕሮግራምና CR WaSH የሚተገበሩ ናቸው። ውል የተገባባቸው ኮንትራክተሮች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ በሚሰሩ ስራዎች ቀደም ሲል ሲሳተፉ የቆዩ በመሆናቸው የካበተ ልምድ ያላቸው መሆኑን ክቡር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ የጠቆሙ ሲሆን አሁንም ስራውን በጥራትና በተቀመጠው የጊዜ ገደብ እንዲያጠናቅቁ በአፅንኦት አሳስበዋል። አማካሪዎቹ በበኩላቸው በተሰጣቸው ዕድል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን አመስግነው ስራውን በወቅቱና በጥራት እንደሚያስረክቡ አረጋግጠዋል።

Share this Post