የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም እየተገመገመ ነው።

የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም እየተገመገመ ነው። መጋቢት 30/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸምን ለመገምገም የተዘጋጀ መድረክ እያካሄደ ነው። የግምገማ መድረኩን በንግግር የከፈቱት በሚኒስትር ዴኤታ ማእረግ የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ክቡር አቶ ሞቱማ መቃሳ ሲሆኑ፣ በእያንዳንዱ ተግባር “ምን ታቀደ፣ ምን ተከናወነ፣ ምን ውጤት ተገኘ” በሚል አግባብ ግልጽ እና ተጨባጭ ሪፖርት እንዲቀርብ አሳስበዋል። አቶ ሞቱማ በተጨማሪም በሚቀርቡ ሪፖርቶች ላይ ጥልቅ ውይይት በማካሄድ በቀሪ ወራቶች ያሉ ክፍተቶችን በመለየት የተሻለ ውጤት ለማምጣት የበለጠ ጥረት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል። በመድረኩ ላይ የቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤቶች የባለፈው ስድስት ወራት ግብረመልስ እና የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶች እንዲሁም የብሔራዊ ጎርፍ መከላከል ፕሮጀክት ፣ የብራይት እና የባዘርኔት ፕሮጀክቶች አፈጻጸም እንዲሁም የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደርና የሀይድሮሎጂና ተፋሰስ መረጃ መሪ ስራ አስፈጻሚዎች እቅድ ክንውን ቀርቧል። ሪፖርቶቹ የአረንጓዴ አሻራ እና የተፋሰስ ልማት ፣ የውሃ አካላት ጥበቃ፣ የውሃ ሀብት ጥራትና ክትትል ፣ የውሃ ምደባና ፈቃድ አሰጣጥ ፣ የመረጃ አያያዝ፣ የጎርፍ መከላከል፣ቅንጅታዊ አሰራር ፣ የአቅም ግንባታ፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች እንዲሁም የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ያሉ ዋና ዋና ጉዳዮችን አካትተው ተዳስሰዋል። ከሰዓት በኋላም በቀረቡ ሪፖርቶች ላይ ሰፊ ውይይት እንደሚካሄድ ተገልጿል። በመድረኩ መጨረሻ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፉ ማጠቃለያ እና የስራ አቅጣጫ እንደሚሰጡ ተጠቅሷል።

Share this Post