በድሪም ፕሮጀክት እየተተገበረ ያለው ሙርቼ ሳይት የሶላር ፓምፕ መስኖና መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ አይነተኛ ሚና እንዳለው ተገለጸ።
አርባምንጭ መጋቢት29 /2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስተር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ ጋሞ ዞን አርባምንጭ ዙሪያ በድሪም ፕሮጀክት እየተተገበረ ያለው የሶላር ፓምፕ መስኖ፣ መጠጥ ውሃ ና የሀይል ፕሮጀክት የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ አይነተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ በድሪሞ ፕሮጀክት እየተተገበረ ያለውና ለመጠጥአርባምንጭ፣ ለመስኖ፣ ለሀይልና ለሌሎች አገልግሎቶችን መስጠት የሚችልና በቅርቡ ተጠናቆ ለአገልግሎት የሚበቃው የጸሀይ ሀይል ሚኒ ግሪድ ጋር በማያያዝ የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የህብረተሰቡን ብልግጽና ለማረጋገጥ አይነተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።
የሶላላር ሚኒ ግሪድ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጡት ክቡር ሚኒስትር ዲኤታው ፕሮጀክቱ ባጠቃለይ ለመስኖ ለመጠጥ ውሃ እንዲሁም የሀይል ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን 250 ሄክታር መሬት በመስኖ የሚያለማና 500 ቤተሰቦችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
የሶላር መስኖእና መጠጥ ውሃ ፓምፕ ፕሮጀክቱ አካባቢው በአትክልትና ፍራፍሬ የሚመረትበት በመሆኑ የጸሀይ ሀይልን በመጠቀም ምርታቸው ሳይበላሽ የሚቆይበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ወደ ተጠቃሚ ለማቅረብ የሚረዳ እንዲሁም ለወጣቶች የስራ እድልን የሚፈጥር ፕሮጀክት መሆኑንም ክቡር ሚኒስትር ዲኤታው ገልጸዋል።
ከ 570 ሚሊዮን ብር ወጪ እየተተገበረ ያለው ፕሮጀክት የአካባቢውን ህብረተሰብ በበቂ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል 14 የውሃ ጉድጓዶች መቆፈራቸውን ገልጸው የመስኖ ስራው 3.85ኪሜ የመስመር ዝርጋታ የተሰራ እና ፕሮጀክቱ 97% እንደደረሰ ጠቁመው በቅርቡ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርም ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱ በዋናነት ከሌሎች የሚለየው ለመስኖ፣ ለመጠጥ ውሃና ለአካባቢው ህብረተሰብ በበቂ ሁኔታ የሀይል ተጠቃሚ ማድረግ የሚችል መሆኑን የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች ገልጸዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ልዩ አማካሪ ክቡር ዶ/ር ቦሾ ቦንጌ፣ የኤስ ኤን ቪ ተወካይ፣ የድሪም ፕሮጀክት ኃላፊዎች የአካባቢው ህብረተሰብ ተገኝተዋል።