ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በኢትዮጵያ የኬንያ አምባሳደርን በቢሯቸው አነጋገሩ።

ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በኢትዮጵያ የኬንያ አምባሳደርን በቢሯቸው አነጋገሩ።   አዲስ አበባ መጋቢት 9/2018 ዓ.ም (ው.ሚ.ኢ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በኢትዮጵያ የኬንያ አምባሳደር ክቡር ገልማ ሙካ ጋር ሁለቱ ሀገራት በጋራ ሊሠሩባቸው በሚገቡ የዘርፉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።   የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ አምባሳደሩ በጋራ ለመስራት ለውይይት በመምጣቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፣ እንኳን ደህና መጡ ብለዋል። ክቡር ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ከኬንያ ጋር ያላት ግንኙነት ታሪካዊ ብቻ ሳይሆን በደም የተሳሰረ ቤተሰባዊ ግንኙነት ያለው መሆኑን በአጵንኦት ገልጸዋል።   አክለውም፣ ክቡር አምባሳደሩ በጠቀሷቸው የመሠረተ ልማት ዘርፎች ከተሠሩት ሥራዎች ባሻገር፣ ለሁለቱም ሀገራት ሕዝቦች ምቹ የሆነ ተጨማሪ የትብብር ሥራዎች መሥራት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። አያይዘውም የመሠረ ልማት ዝርጋታዎችና የግድብ ግንባታ የሀገሪቷ ህግ በሚፈቅደው አግባብ የሁለቱንም ሀገራት ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ የሚከናወን መሆኑን አስገንዝበዋል።   አምባሳደር ገልማ ሙካ ቦሮ በውይይቱ ወቅት ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ታሪካዊና ባህላዊ ትስስር አጉልተው ገልጸዋል። እንደ አምባሳደሩ ገለጻ ሁለቱ ሀገራት ከታሪክ፣ ከባህልና ከቋንቋ ባለፈም የደም ትስስር ያላቸው በመሆኑ ሕዝቦቻቸው እንደ አንድ የተገመዱ ናቸውም ብለዋል። ይሁን እንጂ የሕዝቦቹ ጠንካራ ትስስር ቢኖርም በሀገራቱ መካከል ያለው የመሠረተ ልማት ትስስር ግን በቂ አለመሆኑን ጠቁመዋል።   በተለይም በንግድ፣ በመንገድ፣ በቴሌኮሙኒኬሽን እንዲሁም በውሃና ኢነርጂ መሠረተ ልማት ዘርፎች ያለው ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበለጠ በትብብር መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ የኢነርጂ ተደራሽነቱ ከአፋሪካ ተሻጋሪ መሆኑን ገልፅው በክቡር አምበሳደሩ የቀረቡ የመሠረተ ልማት ትስስርና ግድብ ስራዎች የሀገሪቱ ፓሊሲ በሚፈቅደው አግባብ የኢትዮጵያን ጥቅም በሚያ ስከብር መልኩ የሚከናወን ይሆናል ብለዋል።   በውይይቱ የኬኒያና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮች ተሳተፈዋል።

Share this Post