ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ጋጮ ባባ እና ሌሎች ወረዳዎች በበልግ ዝናብ ምክንያት በተከሠተው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸው ላለፈ ዜጎቻችን የተሰማኝን ኀዘን እገልጻለሁ ብለዋል።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ጋጮ ባባ እና ሌሎች ወረዳዎች በበልግ ዝናብ ምክንያት በተከሠተው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸው ላለፈ ዜጎቻችን የተሰማኝን ኀዘን እገልጻለሁ ብለዋል። አክለውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግሥት ለተጎጂ ወገኖቻችን አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጉን ይቀጥላል ሲሉም በቦታው ሀዘናቸውን በገለፁበት ወቅት ገልፀዋል ። በተጨማሪም ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት እንዲቻል ተገቢው ጥናትና ሥራ መከናወን አለበት በማለት አሳስበዋል። በመጨረሻም ክቡር ጠቅላይ ሚንስተር ዶ/ር አብይ አህመድ የጥንቃቄ ተግባራትም አስፈላጊዎች ናቸው በማለት ለህብረተሠቡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

Share this Post