የአንድ ቋት ብሄራዊ ዋሽ ፕሮግራም የሁለተኛው ፌዝ የስድስት ወር የፕሮጀክት አፈጻጸም ጥሩ ውጤት ማስመዝገቡ ተገለጸ፡፡
መጋቢት 3/2018 ዓም (ው.ኢ.ሚ) የአንድ ቋት ብሄራዊ ዋሽ ፕሮግራም የሁለተኛው ፌዝ የስድስት ወር አፈጻጸምን በተመለከተ የፕሮጀክት ድጋፍ ሠጪ ድርጂቶች ባደረጉት ምልከታ ከባፈው የተሸለ ጥሩ ውጤት ማስመዝገቡን ገልጸዋል፡፡
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶክተር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ድጋፍ ሰጪ ድርጂቶች ባቀረቡት ሪፖርት መደሰታቸውን ገልጸው የተመዘገበው ውጤት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራርና ባለሙያ የCWA II የትግበራ ሂደትን እና ሰፊውን የOWNP ግምገማ፣ቁልፍ ስኬቶችን፣ ተግዳሮቶችን እና የተማሩትን ትምህርቶች መለየት፣በሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ ክልሎች እና አጋሮች መካከል ቅንጅትን ማጠናከር እና ዘላቂ ሁሉን አቀፍ እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የዋሽ አገልግሎት አቅርቦትን ለማፋጠን ቅድሚያ ሰጥቶ በመስራታቸው የተገኘ ውጤት ነው ብለዋል፡፡
ክቡር ዶክተር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ የአንድ ቋት ብሄራዊ ዋሽ ፕሮግራም የሁለተኛው ፌዝ ያለፈው የስድስት ወር ትልቅ ለውጥ ያመጣንበትና ሁሉም ፕሮጀክቶች ላይ ጠንካራ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ስራዎች ሁሉ ከ50 ፐርሰንት በላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የአንድ ቋት ብሄራዊ ዋሽ ፕሮግራም የሁለተኛው ፌዝ የስድስት ወር አፈጻጸምን በተመለከተ የፕሮጀክት ድጋፍ ሠጪ ድርጂቶች የደረጉትን ምልከታ ሪፖርት ለሚመለከታው አካላት ያቀረቡ ሲሆን እየተተገበሩ ያሉ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ከባለፈው የተሸለ ጥሩ አፈጻጸም ላይ መሆናቸውን ገልጸው በቀጣይ ከዚህ በበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል ይገባል ብለዋል።
የብሔራዊ ዋን ዋሽ አስተባባሪ አቶ አብይ ግርማ ከዚህ በፊት ከፌደራል ጀምሮ ያሉ ሴክተሮች ያለውን የስራ አፈጻጸም ወደ መስክ በመውረድ በመገምግም ወደ ኋላ የቀሩትን ችግሮች በመለየትና በመፍታት፣ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል ፕሮግራሙ በተያዘለት ጊዜ እንዲያልቅ እየተሰራ መሆኑን አውስተው፤ባለፈው ስድሰት ወር ጥሩ ውጤት የታየበትና ብዙ ፕሮጀክቶች ውል ተገብቶላቸው ወደ ስራ በመግባት ከ50ፐርሰንት በላይ ውጤት ማምጣታውን ገልጸዋል ፡፡
አቶ አብይ ስራውን ከሚመለከታቸው ሴክተሮች ማለትም ከውሃ፣ ከጤና፣ ከትምህርት፣ ከፋይናንስ እንዲሁም ፕሮግራሙን ከሚደግፉ አጋር ድርጅቶች፤ አለም ባንክ፣ የእንግሊዝ መንግስት፣ ዩኒሴፍ፤ ጋር በመሆን ግባችን ያለፈውን አፈፃፀም መገምገም ብቻ ሳይሆን ለወደፊቱ መንገዱን በማጽዳት የስርዓት ማነቆዎች በመፍታት የCWA IIን ስኬት በማረጋገጥ ወደ ሚቀጥለው የፕሮግራሙ ምዕራፍ ለመቀጠል የሚያስችል ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ ከጤና፣ ከትምህር ፣ከፋይናስና ከውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ ሚCWA II የልማት አጋሮች እና የዋሽ ዘርፍ የተውጣጡ ከፍተኛ አመራሮችና ተሳትፈውበታል፡፡