የአቅም ግንባታ ስልጠናው በኢነርጂ ዘርፉ ሙያዊ እገዛ ለማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተሳታፊዎች ገለጹ።

የአቅም ግንባታ ስልጠናው በኢነርጂ ዘርፉ ሙያዊ እገዛ ለማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተሳታፊዎች ገለጹ።   የካቲት 27/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በታዳሽ ኢነርጂ ተለዋዋጭ የትግበራ ዕቅድ ላይ ትኩረት አድርጎ በራማዳ ሆቴል ለአራት ቀናት የዘለቀው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በኢነርጂ ዘርፍ ለሚከናወኑ ተግባራት ሙያዊ እገዛ ለማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተሳታፊዎች ገለጹ።   የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የሃይል አቅርቦት ዕቅድ ከፍተኛ ባለሙያ የሆነችው እመቤት ቶልቻ ስልጠናው ከሙያችን ጋር ከፍተኛ ግንኙነት ያለውና በሃይል አቅርቦት ዘርፍ ለምናዘጋጀው ዕቅድ አዳዲስ ቁም ነገሮችን አስጨብጦናል ያለች ሲሆን ተከታታይነት ባለው ሁኔታ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም አስተያየቷን ለግሳለ።   ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተሳተፈው የኢነርጂ ኤክስፐርት ኤብሳ ረጋሳ በበኩሉ ኢነርጂን በአግባቡ ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በአግባቡና በጥንቃቄ ማቀድ እንደሚገባ ከስልጠናው እንደተማረና ለዕቅድ ዝግጅት ጠቃሚ የሆኑ አዳዲስ ሞዴሎችን እንዴት ማካተት እንዳለብኝም ተገንዝቤያለሁ ብሏል።   በማሰልጠን ሂደቱ ሚና የነበራቸው በዓለም አቀፉ የታዳሽ ኢነርጂ ኤጀንሲ /IRENA/ የፕሮግራም አስተባባሪ ሚስተር ሂማሊያ ቢር ሽሬስታ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የታዳሽ ኢነርጂ ዘርፉን ለማዘመን ለምታደርገው ጥረት ስልጠናው ጉልህ ሚና እንደሚኖረው፣ተሳታፊዎቹ በነበራቸው ቆይታም በትኩረት ሲከታተሉ መቆየታቸውንና ያገኙትን ግንዛቤ ወደ ተግባር መቀየር ይጠበቅባቸዋል ሲሉም አሳስበዋል።   ስልጠናውን በጋራ ያዘጋጁት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርና የዓለም አቀፉ የታዳሽ ኢነርጂ ኤጀንሲ /IRENA/ ሲሆኑ በቁጥር 20 ለሚደርሱ ተሳታፊዎች በአግባቡ በማጠናቀቃቸው ሰርተፊኬት ተዘጋጅቶላቸዋልም ተብሏል።

Share this Post