በጣሪያ የፀሐይ ኃይል ልማት ብሔራዊ መመሪያ ላይ ውይይት ተደረገ።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባዘጋጀው የጣሪያ የፀሐይ ኃይል ልማት መመሪያ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያዬ፡፡
የካቲት19/2018 ዓም (ው.ኢ.ሚ) በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ ውይይቱ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውና ከፍተኛ ጠቀሜታ ባለው የጣሪያ የፀሐይ ኃይል ልማት እና አጠቃቀም ብሔራዊ ሰነድ ላይ ለመወያየት እና ለማጥራት ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በዓለማችን የኢነርጂ ዘርፍ በከፍተኛ ሁኔታ የሚታይ ለውጥ እያሳየ ሲሆን ይህም ለሃገራችን የኢነርጅ እድገት ከፍተኛ አስተዋፆ የሚያደርግ ነውም ብለዋል፡፡
ሚኒስትር ዲኤታው በማከል ሀገራችን ኢትዮጵያ በፈጣን የኢኮኖሚ እድገት፣የከተማ መስፋፋት እና የሕዝብ ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ አስተማማኝ፣ ተመጣጣኝ እና ቀጣይነት ያለው የኢነርጂ ተደራሽነት ክፍተት እና የአቅርቦት እጥረት ለመፍታት የታዳሽ ኀይሎችን መጠቀም አይነተኛ መፍትሄ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም ኢትዮጵያ ከወንዞቿ፣ ከንፋስ እስከ ፀሐይ ብርሃንዋ ድረስ እጅግ በጣም ከፈተኛ ታዳሽ የኢነርጂ ሀብት የታደለች በመሆኗ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ለጣሪያ የፀሐይ ኃይል ልማት ብሔራዊ መመሪያ አዘጋጂቶ ለውይይ ያቀረበ ና ይህን ረቂቅ ሰነድ ሊተገበር የሚችል እና ተፅዕኖ የሚፈጥር ብሔራዊ መመሪያ የእናንተ ግብረመልስ አስፋላጊ በመሆኑ ይህን እድል በመጠቀም በኢትዮጵያ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም አመቺ ለሆኑ መኖሪያ ቤቶች፣ የግል እና መንግስት ተቋማት ለብሔራዊ የኃይል ደህንነታችን የበኩላቸውን የሚያበረክቱበት ቤተሰቦች፣ ትምህርት ቤቶች እና ኢንዱስትሪዎች በኃይል ስርዓቱ ውስጥ ንቁ ተሳታፊዎች የፀሐይ ኃይል በመጠቀም ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ብሩህ፣ የበለጸግ እና ዘላቂ የሆነ ሀገር እንድንፈጥር ትኩረት ሰጥታችሁ እነድትወያዩበት አሳስባለሁ በማት መርሀ ግብሩን አስጀምረዋል፡፡
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ሀብት ጥናት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሌብ ታደሰ ለጣሪያ የፀሐይ ኃይል ልማት ብሔራዊ መመሪያ ያሰፈለገው በዋናነት የኢነርጂ ተደራሽነት ክፍተትን ለመሙላት፣ኢነርጂ ደህንነትን እና ኢኮኖሚያዊ ምርታማነትን ማሳደግ፣ የብሔራዊ ተጋላጭነትን መቋቋም መገንባት፣ ስማርት የከተማ ልማትን ለማስተዋወቅ እና ሌሎች ተቀሜታዎች እንዳት ገልጸዋል፡፡
ፕሮግራሙ ላይ መመሪያው የቀረበ ሲሆን ሰፊ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ተቆጣጣሪዎች፣ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተወካዮች፣ አልሚዎች እና የግል ሴክተር፣ ፋይናንስ ተቋማት እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈውበታል፡፡