ለፕሮጀክቶች ውጤታማነት የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራርና የህብረተሰቡ ቁርጠኛ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ።
የካቲት /2018 ዓ/ም ውኢሚ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በባዜርኔት /BaSRINET/ፕሮጀክት የሚተገበር የኢብሮ ሰዴን ማህበረሰብ ንዑስ ተፋሰስ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ የአካባቢውንህብረተሰብ በማስተባበር በእርከን ቁፋሮ ስራ ተጀምሯል።
በኢብሮ ሰዴን ተራራ ላይ የእርከን ቁፋሮ ስራ የተጀመረው የባዜርኔት /BaSRINET/ፕሮጀክት አስተባባሪ፣የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና የፕሮጀክቱ የዘርፉ ባለሙያዎች ፣ ከግብርና ሚኒስቴር በየደረጃው ያሉ የተፈጥሮ ሀብትና የመስኖ ባለሙያዎች፣ ስራውን በባለቤትነት የሚያስቀጥሉ የወረዳውና የቀበሌው ባለድርሻ አካላት ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን ነው።
ከግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሀብት ባለሙያ አቶ ዳዊት ዓለሙ ስራው የጋራ መሆኑን ገልፀው ለፕሮጀክቶች ውጤታማነት የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራርና የህብረተሰቡ ቁርጠኛ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል ።
የአካባቢው ነዋሪዎችም የተፋሰሱ የልማት ስራ ወደ ትግበራ ምዕራፍ በመድረሱ እና ወደ እርከን ቁፋሮ በመገባቱ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ወደፊትም ስራውን በባለቤትነት በማስቀጠል ተጠቃሚ የመሆን
ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል።
በዕለቱ በስራው ላይ የተሳተፉ እናቶች ፕሮጀክቱ አካባቢያቸውን እንዲያለሙና፣ የአፈርና የውሃ ጥበቃ ስራ በመስራት የጎርፍ አደጋን እንዲከላከሉ ላቀረበላቸው እድል አመስግነው የበለጠ ውጤታማ ለመሆን የተሻለ የውሃ አቅርቦት እንደሚያስፈልጋቸው ገልፀው እንዲመቻችላቸውም ተማጽነዋል።
የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች ለአካባቢው ማህበረሰብ ዘላቂና ቀጣይነት ያለውን ውሃ ተደራሽ ለማድረግ የአማካሪዎች የውል ጨረታ በሂደት ላይ እንደሚገኝና ስራው እንዲፋጠን የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።
የእርከን ቁፋሮውና ሌሎች የአፈርና ነው ጥበቃ ስራዎች የአከባቢውን ህብረተሰብ በማስተባበር በቀጣይ ተከታታይ ቀናት እንደሚከናወንም ተገልጿል ።