በስምጥ ሸለቆ ሀይቆች የተሰራው የጎርፍ መከላከል ስራ ላይ የመስክ ምልከታ ተካሄደ፡፡

በስምጥ ሸለቆ ሀይቆች የተሰራው የጎርፍ መከላከል ስራ ላይ የመስክ ምልከታ ተካሄደ፡፡   በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ጎርፍ መከላከል ፕሮጀክት በስምጥ ሸለቆ ሀይቆች በአርባ ምንጭ ከተማ የኩልፎ ወንዝ ላይ የተሰራው የጎርፍ መከላከል የማስተካኪያ ስራ የመስክ ምልከታ ተካሄደ፡፡   የካቲት/2018 ዓ.ም(ዉ.ኢሚ) አርባምንጭ በመስክ ምልከታው ወቅትም በፕሮጀክቱ የተሰሩ አጠቃላይ የማስተካከያ ስራዎች በተመለከተ ከቴክኒካል ስራዎች፣ አከባቢያዊና ማህበራዊ ተጽዕኖን ከማረጋገጥ አንጻር የተከናወኑ ተግባራት እንዲሁም ከዕቅዱ አንጻር የተሰሩ ስራዎችን አስመልክቶ የዓለም ባንክ ቡድን ም/መሪ የሆኑት አቶ ድንቅነህ ተፈራ ፕሮጀክቱ ከዚህ በፊት በተደረገው ጉብኝት በተሰጠው የማስተካከያ ሀሳብ መሰረት መሰራቱ ገልጸው በቀጣይ የተሰራውን ስራ ከማጠናከር እና ዘላቂ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ስራዎችን በተመለከተ በተሰራው የዲዛይን ስራ ላይ ተካተው መሰራት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡   በጉብኝቱ ላይ የፕሮጄክቱን አፈጻጸም እና ባለፈው በተሰጠው ግብዓት መሰረት መስተካከሉን የገለጹት አማካሪው በቀጣይ ሊሰሩ የታሰቡ የዘላቂ የጎርፍ መከላከል ስራ በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ አማካሪው ባቀረቡት ገለጻ እና ማብራሪያዎች ዙሪያ ከዓለም ባንክ ቡድን እና ከተሳታፊዎች ገንቢ አስተያየቶች የሰነዘሩ ሲሆን በቀጣይ በፕሮጀክቱ ሂደት ለሚኖረው ትግበራ በከተማ መስተዳደሩ ከሚሰራው የወንዝ ዳር ልማት ጋር አዎንታዊ ግብዓት እንደሚኖራቸውም ተጠቁሟል።   የኢትዮጵያ ጎርፍ መከላከል ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ተመስገን ከተማ ተጨማሪ በተሰሩት ስራዎች እና ቀጣይ በሚሰራው ስራ ላይ ማብራሪያ በመስጠት የተነሱ ሀሳቦችንም ለቀጣይ ስራ እንደግብዓት እንጠቀምበታለን ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።   በጉብኝቱ ላይ የዓለም ባንክ ልዑካን ቡድን፣ ከአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር እና ከአማከሪ ድርጅት እና የኢትዮጵያ ጎርፍ መከላል ፕሮጀክት በጋር በመሆን የመስክ ምልከታውን አካሄደዋል።

Share this Post