በምእራብ ሃረርጌ ዞን ቡርቃ ዲምቱ ወረዳ የሃሮ ጉራቲ እና የቡርቃ ኦዳ ሶላር ሚኒ ግሪድ ፕሮጀክት ታሪክ የቀየረ በጨለማ የተገኘ ብርሀን መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ።

በምእራብ ሃረርጌ ዞን ቡርቃ ዲምቱ ወረዳ የሃሮ ጉራቲ እና የቡርቃ ኦዳ ሶላር ሚኒ ግሪድ ፕሮጀክት ታሪክ የቀየረ በጨለማ የተገኘ ብርሀን መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ። የካቲት2/2018 ዓ/ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በመተባበር በምእራብ ሃረርጌ ዞን ቡርቃ ዲምቱ ወረዳ የሃሮ ጉራቲ እና የቡርቃ ኦዳ ሶላር ሚኒ ግሪድ ፕሮጀክት ታሪክ የቀየረ በጨለማ የተገኘ ብርሀን መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።   በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ኤሌክትሪፍኬሽን ዘርፍ የአደሌ ፕሮጀክት እና የአፍሪካ ልማት ባንክ አስተባባሪ አቶ አዲስ ዓለም መብራቱ የኤሌክትሪ ፍኬሽን የተያዘውን እቅድ ለማሳካት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸው በአፍሪካ ልማት ባንክ የገንዘብ ድጋፍ 25 ሚኒ ግሪድ ፕሮጀክቶችን በመገንባት በጣም ገጠራማ አካባቢ ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።   በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክና ብርሃን ተደራሽነት /Access to Distributed Electricity and Lighting in Ethiopia (ADELE) ፕሮጀክቶች በዋናነት ከግሪድ ውጪ በሆኑ ቴክኖሎጂዎችየኤሌክትሪፊኬሽን ስራዎችን ለማከናወን ተቀርፆ በመተግበር ላይ ይገኛሉ በማለት የፕሮጀክቶቹ ዋና ዓላማም በመላው ሀገሪቱ ለቤተሰብ፣ ማህበራዊ ተቋማት እና ለንግድ ድርጅቶች አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ማድረግ ነውም በማለት አስተባባሪው ገልጸዋል።   ፕሮጀክቱ በዋናነት የገጠር ማህብረሰቦችን የኤሌክትሪክና ብርሃን ተደራሽነትን ለማስፋት ከዋናው የኤሌክትሪክመስመር (ግሪድ) በርቀት ላይ የሚገኙ የገጠር ከተሞችንና መንደሮችን በፀሐይ ሀይል ማመንጫ በመገንባት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ትኩረት ተሰጥቶት እየተከናውኑ መሆኑ እያስመረቅናቸው ያሉ ፕሮጀክቶች ማሳያ ናቸው ብለዋል። በምእራብ ሃረርጌ ዞን ቡርቃ ዲምቱ ወረዳ የሃሮ ጉራቲ እና የቡርቃ ኦዳ ሶላር ሚኒ ግሪድ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኩል የተተገበረ ሲሆን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዋናነት ፕሮጀክቱን በማስተባበር፣ በመምራትና በመከታተል ለፍጻሜ ማድረሱን ገልጸዋል።   የቡርቃ ኦዳ ቀበሌ ነዋሪ ወ/ሮ ኢፍቱ ኦሳ በበኩላቸው የጸሀይ ሀይል ማመንጫው በጨለማ የተገኘ ብርሀን መሆኑን ጠቅሰው አካባቢያቸው ነዋሪዎች በተለይ የሴቶችን ማህበራዊ እና የጤና ችግሮችን የፈታ ኑሯችንን ያቀለ ነውም ብለዋል። ከዚህ ባሻገር የአካባቢው ማህበረሰብ በመረጃም ሆነ በሌላ ገነር እጅግ ወደ ኋላ የቀረ ነበር አሁን ላይ በዚህ ፕሮጀክት ከሌሎች እኩል ሆነናል በማለት ወ/ሮ ኢፍቱ ገልጸዋል።   አቶ አብዲ አደም ፕሮጀክቱ የአካባቢያችን ታሪክ የቀየረ እንዲሁም ለወጣቶች የስራ እድልን የፈጠረ ነው ብለዋል። አቶ አብዲ ፕሮጀክቱ ለአካባቢው ህብረተሰብ ተጠቃሚ የሚያደርግ በመሆኑ ለከተማችን መነቃቃትን የሚፈጥር ነው በማለት ገልጸዋል።   ፕሮጀክቱን የሰሩትን አካላት በማመስገን ሁሉም ህብረተሰብ እንደ ግል ንብረቱ በመንከባከብ ጠብቀው እንደሚይዙት በመግለጽ ፕሮጀክቱ ምን ያክል አስፈላጊ እንደሆነ አቶ አብዲ ተናግረዋል። በሃሮ ጉራቲ በ160 ሚሊዮን ብር ከ703 በላይ ብር ወጪ ከመንግስት፣ አለም ባንክ እና ከሌሎች የገንዘብ ምንጮች የተተገበረና ከ507 በላይ አባወራዎች ተጠቃሚ የሚያደር ፕሮጀክት ሲሆን ለ20 ዓመት አግልግሎት የሚሰጥ ነው።

Share this Post