ፕሮጀክቱ ለዘመናት የቆዬ ችግራቸውን እንደሚፈታላቸው ገለጹ።
ጥር/2018 (ው.ኢ.ሚ) የውሀና ኢነርጅ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በመተባበር በኦሮሚያ ክልል የምእራብ አርሲ ዞን ናንሰቦ ወረዳ የተገነባው የጸሀይ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ለዘመናት የቆዬ ችግራቸውን እንደፈታላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
የናንሰቦ ወረዳ ነዋሪ የሆነችናውና በሆቴል ስራ የምትተዳደረው ወ/ሮ አሰሱ ገዛኸኝ አሁን ላይ የዚህ ፕሮጀክት መተግበር የመብራት ፍላጎትን ብቻ ሳይሆ ዘርፈ ብዙ ማህበራዊ እና ከጤና ጋር ተያያዠ የሆኑ ችግሮችን እንደሚፈታላቸው ገልጸዋል።
ወ/ሮ አሰሱ በማከል ፕሮጀክቱ በተለይ ለሴቶች የሚያባክኑትን ጊዜና በማገዶ ለቀማ በሸክም ምክኒያት የሚደርስባቸውን ከፍተኛ የጤና ችግር ሙሉ በሙሉ በማስቀረት ጤናማ ማህበረሰብ በመፍጠር የደን መጨፍጨፍን በማስቀረት ከጭስ ጋር የሚፈጠረውን የጤና ችግር የአየር ብክለት የሚያስቀር መሆኑን በመግለጽ በፕሮጀክቱ ትግበራ የተሳተፉትን አካላትን አመስግነዋ።
ፕሮጀክቱ ለወረዳዋ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንደሚሰጥና በተለይ ለትምህርት ቤቶች ፣ ለጤና ተቋማት እንዲሁም ለወረዳዋ እድገት ልማቱ እንዲፋጠን ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳለው ወ/ሮ አሰሱ ገልጸዋል፡፡
ሌላኛው የአካባቢው ተወላጅና ነዋሪ አቶ ዳሜ ደቀባ በዘመናቸው ያልነበረ በሩቅ የሚያዩት ወደ አካባቢያቸው በመምጣቱ መደሰታቸውን ገልጸው ይህን ከጨለማ ያወጣቸውን ፕሮጀክት በአግባቡ ለሁሉም ህብረተሰብ መዳረስ እንዲችልና በፍትሀዊነት ሁሉም ነዋሪ ተጠቃሚ እንዲሆን የአገልግሎት ክፍያውን በመክፈል ፕሮጀክቱን ለመጠበቅ የከተማው አስተዳደር እና ህብረተሰቡ በጋራ መስራት ይጠበቅበታል በማለት አስተያየትም ሰጥተዋል።
ፕሮጀክቱ ከአለም ባንክ በተገኘ ገንዘብ በ100 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባና ለ20 አመት የሚያገለግል ሲሆን 824 የህብረተሰብ ክፍሎችን የሀይል ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው።