የሶላር ሚኒግሪድ ስራዎችን በህብረት ስራ ኤጀንሲዎች ለማስተዳደር የሚያስችል ስልጠና እየሰጠ ነው።

የሶላር ሚኒግሪድ ስራዎችን በህብረት ስራ ኤጀንሲዎች ለማስተዳደር የሚያስችል ስልጠና እየሰጠ ነው። በአፍሪካ ሚኒ ግሪድ ፕሮግራም ስር UNDP/GEF ኢትዮጵያ ብሔራዊ የቻይልድ ሚኒ ግሪድ ፕሮጀክትን በህብረት ስራ ለማስተዳደር የሚያስችልና አመራር ላይ የተመሰረተ የሚኒ ግሪድ ቴክኖሎጂ ልማት ስልጠና እየሰጠ ነው።   21/04/2018ዓም(ው.ኢ.ሚ) በመርሀ ግብሩ ለይ የተገኙት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የዩኤንዲፒ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ይመስላል ተፈራ ስልጠናው በዋናነት የአፍሪካ ሚኒግሪድ ፕሮግራም UNDP ፕሮጀክት የሚተገብራቸው ሚኒ ግሪዶች በህብረት ስራ ሞዴል መሆኑን ገልጸው እነዚህ በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች የሚገኙ ህብረት ስራዎችን በማደራጀት በሚኒግሪድ ዙሪያ ያላቸውን መረዳት ለመጨመር ስራውን ለማስተዳደር እና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ በባለቤትነት እንዲይዙት ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል።   አቶ ይመስላል ስልጠናው በዋናነት ፕሮጀክቱ ከመተግበሩ በፊት ወሳኝ የሆኑ ክፍተቶችን ለህብረት ስራው አባላት አቅማቸውን ለመገንባት በኢነርጂ ቢሮች እና በህብረት ስራው ከክልል እስከ ወረዳ ላሉ አደረጃጀቶች አንድ ላይ በማድረግ ከሁለቱም በኩል ግንዛቤ መፍጠር ነውም ብለዋል፡፡ አቶ ይመስላል በማከል እንዚህ ሁለት ተቋማት በጋራ ሊሰሩ ስለሆነ በዘርፋቸው ስልጠና በመውሰድ ልምድ በመለዋወጥ ቀጣይ ስራ እንዴት መተግበር እንደሚገባውና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ በሚችሉበት መንገድ ስልጠና እወሰዱ እንደሆነም አስተባባሪው ገልጸዋል፡፡   በመጨረሻም አቶ ይመስላል ስራውን በታቀደው መሰረት በትብብር እና በመደጋገፍ በመስራት ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ገልጸው ሰልጣኞች በሁለቱም ወገን በጥልቀት በመከታተል ወደ ተግባር ሲገባ ስራውን ውጤታማ ለማድረግ ስለሚረዳ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡ በህብረት ስራ ኮሚሽን ህብረት ስራ ማህበራት ማጠናከርና ማዘመን ዴስክ ኃላፊ አቶ አበበ አለማየሁ ከፕሮጀክቱ ጋር በተገናኘ ፕሮጀክቱ ከህብረት ስራው ጋር በማገናኘት ህብረተሰቡ ተጠቃሚ የሚሆንበትን መንገድ ማመቻቸት አላማ አድርገው ለመስራ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡   የሱማሌ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፋ አቶ ሙሀሙድ መሀመድ በክልላቸው ሲሰሩ የነበሩ የሶላር ግሪዶች በመንግስት በኩል ይተዳደሩ እንደነበር ገልጸው አሁን ላይ በህብረት ስራ መተላለፉ ጥሩና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በቅርበት የሚያረጋግጥ በመሆኑ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጅ ነን ብለዋል።   በተመሳሳይ የኦሮሚያ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ሶሬሳ ስራውን በመተባበር ለመስራ ዝግጁነታቸውን ገልጸው ስራው ሲተገበር ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ከህብረት ስራው ጋር በጋራ ለመፍታት የበኩላቸውን ጥረት እንደሚያደርጉና አስፈላጊ በሆኑ ነገሮች ሁሉ ከህብረት ስራው ጎን እንደሚሆኑ ገልጸዋል፡፡ በስልጠናው ላይ ከኦሮሚያና ከሶማሊያ ክልሎች የተውጣጡ ባለሙያዎች የሕብረት ስራ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡

Share this Post