ለአንድ ተቋም ውጤታማነት ቅንጅታዊ አሰራርና መናበብ ወሳኝ እንደሆነ ተገለጸ።

ለአንድ ተቋም ውጤታማነት ቅንጅታዊ አሰራርና መናበብ ወሳኝ እንደሆነ ተገለጸ።

አዳማ መስከረም 13/2018 ዓ.ም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በቅጅታዊ አሰራርና ተናቦ በመስራት ላይ ከቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤቶች ጋር የጋራ ምክክር አደረገ።

የምክክር መድረኩን በንግግር የከፈቱት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ለአንድ ተቋም ውጤታማነት ከታችኛው ፈፃሚ እስከ ከፍተኛ አመራር ድረስ ቅንጅታዊ አሰራርንና መናበብን ማስፈን ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።

በ2018 በጀት እንደተቋም በሁሉም የቤዝን አስተዳደር ጽ/ቤቶች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የጣለውን ግብ እንደሀገር ለማሳካት ከ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለፈ ከክልሎች ጋር መቀናጀትና መናበብ እንደሚያስፈልግ አሳስበው፤ ቅንጅቱም በሀብት አጠቃቀም፣ በመረጃ አያያዝ፣ በመረጃ አቀራረብና ፍሰት መደበኛ ስራዎች ከፕሮጀክቶችና ከባድርሻ አካላት ጭምር መሆን እንዳበት ገለጸዋል፡፡ በተጨማሪም አሰራርን ለማቀናጀት ከተለመደው አሰራር ወጥተን ዘመናዊ አሰራርና ግልፀኝነትን በመከተል መፍጠንና መፍጠር እንደሚጠበቅ አሳስበዋ።

አክለውም የቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤቶች በመቀናጀትና የአሰራር አቅምን በማሳደግ ተወዳዳሪ በመሆን የተመደበውን ሀብት በአግባቡ በመጠቀምና ለታለመለት አላማ ብቻ በማዋል ተቋሙ የጣለውን ግብ ያነገበውን ተልዕኮ እንዲያሳካ በፍፁም የኃላፊነት ስሜት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ከአደራ ጋር አሳስበዋል። በመጨረሻም ለስራው መሳካት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም ገልፀዋል።

በመድረኩ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ዋና ስራ አስፈፃሚ፣ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር መሪ ስራ አስፈፃሚ፣ የሀይድሮሎጂና ተፋሰስ መረጃ መሪ ስራ አስፈፃሚ እና በዘርፉ ላይ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች በፕሮጀክት ባለሞያዎች እንዴት መቀናጀትና እስከ ታች እርከን እንዴት መናበብ እንደሚገባ ፅሁፍ ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጓል።

በምክክር መድረኩ ክቡር ሚኒስትሩን ጨምሮ በሚኒስትር ድኤታ ማዕረግ የክቡር ሚኒስትሩ ልዩ አማካሪ አቶ ሞቱማ መቃሳ፣ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስራ ኃላፊዎች፣ የ3ቱ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

Share this Post