የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የህብረተሰቡን የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር በዘላቂት ለመፍታት እየሰራ መሆኑ ተገለጸ።
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የህብረተሰቡን የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር በዘላቂት ለመፍታት እየሰራ መሆኑ ተገለጸ።
ሀምሌ 3/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብሄራዊ ዋን ዋሽ ፕሮግራም አካል በሆነው በCR-WaSH ፕሮጀክት የሚተገበር የሲራሮ ቦዲዎቾ መጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ግንባታ ለማናወን ከሀቢብ ሁሴን ግንባታና የውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ጋር የውል ስምምነት ተፈረመ፡፡
ከ447 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባው ፕሮጀክት የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የሚያስችል የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ነው፡፡
በስምምነቱ የሲቪል ስራ ግንባታ፣ የቧንቧ እና የመገጣጠሚያ ቱቦዎች ተከላ እና የኤሌክትሮ-ሜካኒካል እቃዎች አቅርቦት እና የውሃ መስመር ዝርጋታን የሚያጠቃልል መሆኑም ተገልጿል።
ስምምነቱን የተፈራረሙት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የህብረተሰቡን የመጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ እየሰራ መሆኑን አውስተው፤ ፕሮጀክቱን በሚፈለገው የጥራት ደረጃና በተቀመጠው የጊዜ ገደብ በማጠናቀቅ የህብረተሰቡ የመጠጥ ውሃ ችግር እንዲፈታ አሳስበዋል።
ክቡር አምባሳደሩ አያይዘውም በዋን ዋሽ ናሽናል ሮግራም በሚተገበረው የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት አካባቢው ዝናብ አጠርና በውሃ እጥረት የሚጠቃ በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጥናት አስጠንቶ ውሃ ያለበትን አካባቢ የለየና የጉድጓድ ቁፋሮ ያለቀ በመሆኑ ግንባታው ከተያዘለት የጊዜ ገደብ ቀድሞ እንዲጠናቀቅ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ፣ በክልሉ መንግስትና በክልሉ ውሃ ቢሮ እና በአካባቢው ማህበረሰብ በኩልም የተለመደው ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡
ሀቢብ ሁሴን የግንባታና የውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ዋና ስራ አስኪያጅ ሸህ ሀቢብ ሁሴን ከዚህ በፊት ከሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ጋር ብዙ ስራዎችን እንደሰሩ ገልጸው ስራውን በጥራትና ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ ባጠረ ቀድመው እንደሚያጠናቅቁ ቃል ገብተዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በ1አመት ከ3 ወር ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ሲበቃ 54 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡