የያያወርቄ የውሃ አቅርቦት ፕሮጀክት የግንባታ ቁጥጥር ውል ስምምነት ተፈረመ::
ሰኔ 23/ 2017 ዓ/ም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የያያወርቄ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ፕሮጀክት የግንባታ ክትትል ውል ስምምነት ከአቤክ ቢዝነስ ግሩፕ ከተባለ አማካሪ ድርጅት ጋር ተፈራረመ።
የግንባታ ክትትል ውሉን የፈረሙት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሚኒስቴር ዴኤታ ማዕረግ የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ክቡር አቶ ሞቱማ መቃሳ ሲሆኑ በአማካሪ ድርጅቱ በኩል የፈረሙት የአቤክ ቢዝነስ ግሩፕ አማካሪ ድርጅት ስራ አስኪያጅ ኢ/ር በእውቀቱ ደስታው ናቸው ።
ፕሮጀክቱ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የያያወርቄ ቀበሌ በ20 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚከናወን የማማከር ስራ ሲሆን በ15 ወር ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ።