በአረንጓዴ ሀይድሮጅንና በባዮፊዩል ልማት ስትራቴጂ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።

በአረንጓዴ ሀይድሮጅንና በባዮፊዩል ልማት ስትራቴጂ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ። ሰኔ 16/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው ባለድርሻዎች ጋር በአረንጓዴ ሀይድሮጅንና በባዮፊዩል ልማት ስትራቴጂ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ። የውይይት መድረኩን ያስጀመሩት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ ኢትዮጵያ በርካታ የታዳሽ ኢነርጂ ሀብት ባለቤት በመሆኗ ግሪን ሀይድሮጅንን ማምረትና መጠቀም የምትችልበት እድል አላት ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ሰፊ ባዮማስ ያላት ሀገር በመሆኗ ግሪን ሀይድሮጅንን በማምረት ታዳሽ ኢነርጂዎች ጥቅም ላይ እንደሚውሉ የገለፁት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው፤ የከርሰምድርና ገፀ ምድር የውሃ ሀብቷን፣ የፀሀይ ሀይል፣ የጂኦተርማልና የነፋስ ሀይልን በመጠቀም ግሪን ኢነርጂን በማምረት ነዳጅ የሚጠቀሙ የትራንስፖርት ዓይነቶችን ለመተካት፣ የአውሮፕላን ነዳጅ ለማምረት፣ ለኢንዱስትሪ እንዲሁም ማዳበሪያን ለማምረት አገልግሎት የሚውለውን የነዳጅ ፍጆታ በማስቀረት ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል ስትራቴጂ ነው ብለዋል፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ የተከለሰው የኢነርጂ ፖሊሲንም መሰረት ያደረገ የግሪን ሀይድሮጅን ስትራቴጂው እንደሀገር ግሪን ሀይደርጅንን አምርቶ ከመጠቀም ባለፈ ኤክስፖርት ለማድረግም ሆነ በዘርፉ የኃይል ትስስር በመፍጠር የጀመርነው ልማት ዕውን በማድረግ ብልፅግናችንን እናረጋግጣለን ብለዋል፡፡ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ሀብት ጥናት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሌብ ታደሰ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ያላትን ውሃ፣ ታዳሽ ኢነርጂና የኤሌክትሮላይዘር ቴክኖሎጂን በመጠቀም አንደሀገር ራስን በምግብ ለመቻል በሚደረገው ጥረት ውስጥ ከውጭ የሚገባን ማዳበሪያ በሀገር ውስጥ ለማምረት ያስችላታል፤ ነዳጅን በመተካት ረገድም ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታል ብለዋል፡፡ ግሪን ሀይድሮጅን ለማምረት የሚያስችለው የኤሌክሮላይዘር ቴክኖሎጂ ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱ ደግሞ በቀላሉ ለማግኘት ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥሯል ያሉት መሪ ስራ አስፈፃሚው ግሪን ሀይድሮጅንን በማምረት ሀገራችን ወደ ተሻለ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል ብለዋል፡፡ ቴክኖሎጂው አዲስ ከመሆኑ ጋር ተያይዞም መንግስት በሰጠው ትኩረት ልክ ሁሉም ባለድረሻ አካላትና እና የግሉ ዘርፍ በምርምርና በስትራቴጂው በመመራት ለተፈፃሚነቱ ኃላፊነትን እንዲወጡ አሳስበው ተቋሙም የሚያስፈልገውን ክትትልና ድጋፍ ያደርጋልም ብለዋል፡፡ በመድረኩ ከየክልሉ የኢነርጂ ቢሮ ኃላፊዎች፣ ከግብርናና ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር፣ ከተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች የታዳሽ ኃይል ማዕከላት፣ የግል ዘርፍና ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻዎች ች ተሳትፈዋል፡፡

Share this Post