በውሃ እና ኢነርጂ ረቂቅ የፖሊሲ ሰነዶች ላይ ማጠቃለያ ውይይት ተደረገ ፡፡
ሰኔ 03/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በተሻሻሉት ረቂቅ የውሃ እና ኢነርጂ ማጠቃለያ ፖሊሲዎች ላይ የማኔጅመንት አባላትን አወያይተዋል ።
ክቡር ሚኒስተሰሩ በመጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን፣ በኢነርጂ ልማት እንዲሁም የሁሉም የጀርባ አጥንት በሆነው የውሃ ሀብት አስተዳደር ላይ በተዘጋው የውሃና ኢነርጂ ረቂቅ ፖሊሲዎች ዙሪያ ከተለያዩ አካላት ጋር ውይይት ተደርጎ በተሰጡ ተጨማሪ ሀሳቦች ላይ ማኔጅመንት አባላቱን አወያይተዋል፡፡
የፖሊሲው ዋና አላማ ያለንን የውሃ ሀብት በአግባቡ ከመጠቀም ባለፈ በዘርፉ የሚነሱ ጥያቄዎችን መመለስ በሚያስችል መልኩ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በላቀ ሁኔታ ማረጋገጥ እንዲቻል ፖሊሲዎቹ አስፈላጊ መሆናቸውን ነው ክቡር ሚኒስትሩ የገለጹት።
ረቂቅ ፖሊሲዎቹ በተለያዩ ጊዜያት ለውይይት ቀርበው የተሰጡ ሀሳብና አስተያየቶችን እንደ ግብአት በመጠቀም ፖሊሲዎቹን ግልጽ በሆነና በማያሻማ መልኩ አገልግሎት ላይ ለማዋል የመጨረሻ ምእራፍ ላይ ደርሰናል ብለዋል።
በውሃ ረቂቅ ፖሊሲው የተስተካከሉ ሀሳቦችን ጨምረው የመጨረሻ ረቂቁን ለማኔጅመንት አባላቱ ያቀረቡት የውሃ ሃብት አስተዳደር አማካሪ አቶ በላይነህ ይርዳው ፓሊሲው በዋናነት ያለንን የውሃ ሀብት በአግባቡ ለመጠቀምና ለማስተዳደር እንዲረዳ ታላሚ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ በኢነርጂ ረቂቅ ፖሊሲው ላይ የተሠጡ አስተያየቶችን በማካተት እና የበለጠ በማጠናከር የሀይል ተደራሽነት እንዲሰፋ እና የኢነርጂ አጠቃቀም ብቃት እና ቁጠባን ለማሳደግ አስቻይ በሆነ መልኩ የቸሻሻለውን ረቂቅ ፖሊሲ ያቀረቡት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አቶ አንዷለም ሴአ ናቸው።
የውሃ እና ኢነርጂ ረቂቅ ፓሊሲዎቹ ከ20 ዓመታት በላይ እንዲያገለግሉ ታሳቢ ተደርገው መዘጋጀታቸውም ተገልጿል፡፡
በውይይቱም የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ እና የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ ተገኝተዋል።