የአንድ ቋት ብሄራዊ ዋሽ ፕሮግራም የሁለተኛው ምዕራፍ የስድስት ወር የመስክ ሱፐርቪዥን በሁሉም ክልሎች እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡

የአንድ ቋት ብሄራዊ ዋሽ ፕሮግራም የሁለተኛው ምዕራፍ የስድስት ወር የመስክ ሱፐርቪዥን በሁሉም ክልሎች እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡ ሰኔ 02/2017 ዓም (ው.ኢ.ሚ) የአንድ ቋት ብሄራዊ ዋሽ ፕሮግራም የሁለተኛው ምዕራፍ የስድስት ወር የመስክ ሱፐርቪዥን ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ባሳተፈ ሁኔታ በሁሉም ክልሎች እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡ የሱፐርቪዥን ስምሪት ቅድመ ዝግጅቱን አስመልክቶ በተካሄደ መድረክ የተገኙት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ከሁሉም ክልሎች በተሰሩ ስራዎች ላይ የቀረቡ ሪፖርቶችን በሚገባ በመመልከት ፣ የመስክ ስራዎችን በግንባር በማየት እና በመገምገም የቀጣይ ስራዎቹ በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ሊያግዝ የሚችል ሪፖርት ማቅረብ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ የብሔራዊ አንድ ቋት ( One WaSH) አስተባባሪ አቶ አብይ ግርማ ተልእኮው ከፌደራል ጀምሮ ያሉ ሴክተሮች የስራ አፈጻጸም በመገምገምና ወደ መስክ በመውረድ እስካሁን የተካሄደውን አፈጻጸም በማየት ወደኋላ የቀሩትን ችግሮች በመለየትና በመፍታት፣ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል ፕሮግራሙ በተያዘለት ጊዜ እንዲያልቅ እንደሚረዳ ገልጸዋል። በመስክ ተልእኮው በሁሉም ክልሎች አንድ ወረዳና አንድ ከተማ እንደሚታይ እና የማጠቃለያ ሪፖርት እንደሚቀርብም አቶ አብይ አክለው ገልጸዋል፡፡ ስራው ከሚመለከታቸው ከውሃ፣ ከጤና፣ ከትምህርት፣ ከፋይናንስ እንዲሁም ፕሮግራሙን ከሚደግፉ አጋር ድርጅቶች፤ አለም ባንክ፣ የእንግሊዝ መንግስት፣ ዩኒሴፍ፤ ጋር በመሆን የእንደሚከናወን ተናግረዋል፡፡ በመርሀ ግብሩ ላይ ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከፋይናንስ ሚኒስቴር የተውጣጡ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም አስተባባሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

Share this Post