የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የጽዱ ኢትዮጵያን አላማ ለማሳካት በውሃ ሀብት ልማት ላይ እና በታዳሽ ኢነርጂ ሀብት ልማት ላይ እንደሚሰራ ተጠቆመ፡፡
ግንቦት 29/2017 ዓ.ም. (ው. ኢ. ሚ) የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ባዘጋጀው ጽዱ ኢትዮጵ ንቅናቄ መድረክ ላይ የተገኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ሡልጣን ወሊ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የጽዱ ኢትዮጵያን አላማ ለማሳካት በውሃ ሀብት ልማት ላይ እና በታዳሽ ኢነርጂ ሀብት ልማት ላይ እንደሚሰራ ተጠቆመ፡፡
ክቡር ሚነስትር ዴኤታው የሀይል አቅርቦትን ሙሉ በሙሉ ከታዳሽ ሀይል ምንጮች ብቻ በማምረት የአካባቢ ደህንነት ማስጠበቅና የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል በ ሚያችል መልኩ እየተሰራ ነው ብለው፤ ጽዱ ኢትዮጵያን እውን ለማድርግ የኢነርጂ ልማት ዘርፉ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ጠቁመዋል፡፡
ዘላቂ የውሃና የሳኒቴስን አቅርቦት መሰረተልማቶችን በማስፋፋት እና የውሃ አካላትን ከደለል በመጠበቅ የውሃ ግኝትን አስተማማኝ በማድረግ የጽዱ ኢትየጵያ ንቅናቄን እንደሚደግፍ ተናግረዋል፡፡
በአጠቃላይ ለብክለት ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን በመለየትና በከተሞች፤ በኢንዱስትሪዎችም ጭምር ወቅታዊ የብክለት ቁጥጥር ማድረግና የእርምት እርምጃዎች እንዲወሰዱ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በጋራ የሚሰራበት አግባብ መኖሩንም ጠቁመዋል፡፡
በቅርቡ በተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀው የውኃ አካል ዳርቻ አወሳሰን፣ልማት እና እንክብካቤ አዋጅ የወንዝ ዳርቻዎችን ለማፅዳትና ለማልማት የሚመጡ ችግሮችን ለማስቀረት የሚያስችልና የተራቆቱ የወንዝች ዳርቻዎችን ለመንከባከብና ለማልማትም የሚያግዝ በመሆኑ ጽዱ አካባቢን ለመፍጠር አይነተኛ መሳሪያ ነው ብለዋል፡፡