ትውልዱ ስለሀገራችን የውሃ ሀብት እንዲያውቅ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ተባለ፡፡

ትውልዱ ስለሀገራችን የውሃ ሀብት እንዲያውቅ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ተባለ፡፡ ግንቦት /2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የዋን ላቭ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ዲጂታል ኤግዚቢሽንን በጎበኙበት ወቅት ትውልዱ ስለሀገራችን የውሃ ሀብት እንዲያውቅ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለፀ፡፡ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ኤልቤቴል ጋሻው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያለበትንና ስለኢትዮጵያ የውሃና የኢነርጂ ሀብት ምን ይመስላል የሚለውን ከማየቴም ባሻገር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ሲመሩ የነበሩትን የቀድሞ ሚኒስትሮች በማወቄ ደስተኛ ነኝ ብላለች፡፡ ተማሪ ኤልቤቴል ውድ የሆነውን የውሃ ሀብት እንዴት መጠበቅና መንከባከብ እንዳለብኝ የተረዳሁበትና በሀይድሮፖለቲክስ ጉዳይም ስለውሃ ሀብታችን ተደራዳሪ ለመሆን አነሳስቶኛል ብላለች፡፡ በዲጅታል ኤግዚቢሽ ማዕከሉ ያየሁት ነገር የወደፊት ህልሜን እንድቀይር አድርጎኛል ያለው የ6ኛ ክፍል ተማሪ ኪሩቤል ከፍያለው ድንበር ተሻጋሪና ድንበር ተሻጋሪ ያልሆኑ ወንዞችን፣ የተለያዩ የተፋሰሱ ሀገራት ስለውሃ የሚረዱበትን አግባብ፣ 12ቱን ተፋሰሶችና ገባር ወንዞቻችንም ለማወቅም ዕድል ፈጥሮልኛል ብሏል፡፡ ምንም እንኳን ሶፍዌር ኢንጂነሪንግ ለመማር ፍላጎት ያለኝ ቢሆንም ዲጅታል ኤግዚቢሽን ማዕከሉን ከጎበኘሁ በኃላ በውሃው ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት አሳድሮብኛል ብሏል፡፡ መምህራኖችም ተማሪዎች በዚህ ልክ ስለውሃ ሀብታችን ጥልቅ እውቀትና የጋራ ግንዛቤ እንዲኖራቸው በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኩል እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡

Share this Post