በውሃ እና ኢነርጂ ረቂቅ የፖሊሲ ሰነዶች ላይ ከባለድርሻ አካላት እና ከልማት አጋር ድርጅቶች ጋር ውይይት እየተደረገ ነው፡፡

በውሃ እና ኢነርጂ ረቂቅ የፖሊሲ ሰነዶች ላይ ከባለድርሻ አካላት እና ከልማት አጋር ድርጅቶች ጋር ውይይት እየተደረገ ነው ፡፡ ግንቦት 18/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በመድረኩ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በተሻሻሉት ረቂቅ የውሃ እና ኢነርጂ ፖሊሲዎች ላይ ንግግር በማድረግ ውይይቱን አስጀምረዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚተግብራቸው ስራዎች በመጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን፣ በኢነርጂ ልማት እንዲሁም የሁሉም የጀርባ አጥንት በሆነው የውሃ ሀብት አስተዳደር ላይ የነበረው ፓሊሲ የቆየ በመሆኑ አሁን ላይ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በላቀ ሁኔታ ለማረጋገጥ የተሻሻሉ ረቂቅ ፖሊሲዎች መዘጋጀታቸውን ክቡር ሚኒስትሩ ገልጸዋል። የውሃ ረቂቅ ፖሊሲው በዋናነት የውሃ ሀብታችን አብዛኛው ድንበር ተሻጋሪ በመሆናቸው ከጎረቤት ሀገራት ጋር መልካም ግንኙነትን ለመፍጠር ፣ ያለንን የውሃ ሀብት በአግባቡ ለመጠቀምና ለማስተዳደር እንዲረዳ ታላሚ ያደረገ ኅጅነው ብለዋል፡፡ የኢነርጂ ረቂቅ ፖሊሲው ደግሞ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ የበለጠ በማጠናከር የሀይል ተደራሽነት እንዲሰፋ የሚያደርግ በመሆኑ በሁለቱ ረቂቅ የፖሊሲ ሰነዶች ላይ በንቃት በመሳተፍ ግብዓት የሚሆን ሀሳብና አስተያየት እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል። የውሃ እና ኢነርጂ ረቂቅ ፓሊሲዎቹ ከ20 ዓመታት በላይ እንዲያገለግሉ ታሳቢ ተደርገው መዘጋጀታቸውም ተገልጿል፡፡

Share this Post