ክቡር ሚኒትሩ ከአለምባንክ ልኡካን ቡድን ጋር ተወያዩ።

ክቡር ሚኒትሩ ከአለምባንክ ልኡካን ቡድን ጋር ተወያዩ። ግንቦት 07/2017 ዓ..ም. (ው.ኢ.ሚ.) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ከአለምባንክ የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር በሚስ. አና ዌሌንስቴይን ከተመራ ቡድን ጋር ተወያዩ፡፡ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ የመጠጥ ውሃ ተደራሽ ለማድረግ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን አንስተው፤ ከ76 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽ ማድረግ መቻሉንና ሙሉ በሙሉ ለዜጎች ተደራሽ ለማድግ ከፍተኛ ጥረት እንደሚይቅ ጠቁመዋል፡፡ ኢነርጂ ልማትን በተመለከተ ለ54 በመቶ ዜጎች የሀይል ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ጠቅሰው፤ ሙሉ በሙሉ ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ ሀብት እደሚጠይቅ ተናግረዋል፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ አክለውም በቀጣይ የግሉ ዘርፍ በመጠጥ ውሃ አቅርቦት ላይ የሚሰማራበትን ሞዳሊቲ የማዘጋጀትና የመተግበር ስራ እንደሚሰራና የውሃ አገልግሎት ተቋማት አቅም ማጎልበት ላይም እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡ ሚስ አና በበኩላቸው በኢትዮጵያ የአንድ ቋት የውሃና ሳኒቴሽን ፕሮግራም (One WASH) አተገባበር መሻሻል የሚታይበት መሆኑን ጠቁመው፤ በመጠጥ ውሃ አቅርቦት ላይ የግሉ ዘርፍ የሚሰማራበትን ሁኔታ ግምት ውስጥ ማስገባት እና የውሃ አገልግሎት ተቋማት የመፈጸም ብቃታቸውን ማሳደግ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ የከርሰምድር ውሃ ጥናትና ፍለጋ ላይ ውጤታማ ስራ መስራት በሚቻልበት ጉዳይና ለመጠጥ ውሃ መሰረተልማት የሶላር ሀይል መጠቀም አስፈላጊነት በውይይቱ ተነስቷል፡፡

Share this Post