የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በውሃው ዘርፍ እየሰራ ያለውን ጠንካራ ስራ ተገንዝበናል ሲሉ ተማሪዎች ገለጹ፡፡
ግንቦት 7/2017ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በውሃው ዘርፍ እየሰራ ያለውን ጠንካራ ስራ ተገንዝበናል ሲሉ የዶክተር ሀዲስ አለማየሁ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ገለጹ፡፡
የውሃና ኢነርጂ መኒስቴር ዲጅታል ኤግዚቢሽን ማዕከልን ስትጎበኝ ያነጋገርናት የ10ኛ ክፍል ተማሪ አርሴማ አፈወርቅ ሀገራችን ያላትን የውሃ ሀብት በሚለካ እና ዘመናዊ በሆነ መንገድ መደራጀቱ ብሎም የህዳሴ ግድብ አሁናዊ ሁኔታ በቀጥታ ማየታችን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በውሃው ዘርፍ ምን ያህል ጠንካራ ስራ እየሰራ እንዳለ ያሳያል ብላለች፡፡
በዚህ አሰራርም ኢትዮጵያ በርካታ ተፋሰሶች ያሏት እንደመሆኑ እንደ ህዳሴ ግድብ ያሉ በርካታ ግድቦችን መገንባት እንደምትችል ተገንዝቤአለሁ ብላለች፡፡
ኢንጅነር የመሆን ህልሟን እውን የሚያደርግ ተግባር በዲጅታል ኤግዚቢሽን ማእከሉ ማየቷን የገለጸችልን ሌላኛዋ የ10ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው አርሴማ ካሳሁን ደግሞ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ያላትን የውሃ ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዲጅታል የውሃ መረጃ አያያዝ ስርዓት በእጅጉ እንዳስገረማትና እንዳስደሰታት ገልጻልናለች፡፡
በውሃው ዘርፍ ምርምር ለሚያርጉ እና የመመረቂያ ጽሁፍ ለሚያዘጋጁ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ጥሩ አጋጣሚ እንደሆነ ነግራናለች፡፡