የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰምድ ውሃ ፕሮጀክት አተገባበር ላይ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ ነው፡፡

የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰምድ ውሃ ፕሮጀክት አተገባበር ላይ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ ነው፡፡ ግንቦት 04/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰምድር ውሃ ፕሮጀክት አተገባበር ላይ በአለምባንክ ቡድን የክትትልና ድጋፍ ስራ እየተከናወነ ነው፡፡ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርና በመስኖና ቆላማ ሚኒስቴር በሚተገበረው የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰምድ ውሃ ፕሮጀክት ላይ ከአለም ባንክ በተውጣጡ ባለሙያች በፕሮጀክቱ አፈጻጸም ላይ የውሃና ኢነርጂ ሚነስቴር የመጠጥ ዉሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ እና የፕሮክቱ አስተባባሪዎችና ኤክስፕርቶች በተገኙበት ውይይት ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም ፕሮጀክቱ ላይ የሚሳተፉ አማካሪዎችና ተቋራጮች ጋር ቀደም ብሎ ውይይት መደረጉ ታውቋል ፡፡ የክትትል እና ድጋፍ ስራው ለሳምንት ያህል የሚቀጥል ሲሆን ፕሮጀክቱ እየተተገበረባቸው በሚገኙ አካባቢዎች የመስክ ምልከታ እንደሚደረግ ከተዘጋጀው መርሃግብር መረዳት ተችሏል፡፡ የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰምድ ውሃ ፕሮጀክት የመጠጥ ውሃ፣ የመስኖና የከርሰምድር ውሃ አቅም ጥናት የተካተተበት ፕሮጀክት ነው፡፡

Share this Post