የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ሉኡካን ቡድን ጋር ተወያየ::

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ሉኡካን ቡድን ጋር ተወያየ:: ግንቦት 04/2017 ዓ/ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጅ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ በኢትዮጵያ ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ምክትል አምባሳደር እና ከማስዳር ካምፓኒ ተወካዮች ጋር ተወያዩ፡፡ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ በኢትዮጵያ የታዳሽ ሀይል ኢነርጂ ልማት ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት እየተተገበረ እንደሚገኝ ገልጸው፤ የታዳሽ ሀይል ልማት ላይ ለመሰማራትም ምቹ ሁኔታዎች መፈጠራቸውን ጠቁመዋል፡፡ በተልይ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት አዋጅ እንደሃገር ድርጅቶች በታዳሽ ኢነርጂ ልማትም ይሁን በሌሎች መስኮች ለመሰማራት ምቹ መደላድል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ልኡካን ቡድን በበኩላቸው የማስዳር ድርጅት በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ታዳሽ ኢነርጂ ላይ በርካታ ስራዎች ማከናወናቸውን ገልጸው፤ በኢትዮጵም መሰል ተግባራት ላይ መሰማራት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡ ልኡካኑ ኢትዮጵያውያን የፈጠራ ሰዎች በዛይድ ሰስተነቢሊቲ ፕራይዝ (Zyed Sustainability Prize) ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሶላር ኢነርጂ ፕሮጀክቶች ላይ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት መፈረማቸው ይታወቃል፡፡

Share this Post