የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከአውስትራሊያ ልኡክ ጋር ተወያየ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከአውስትራሊያ ልኡክ ጋር ተወያየ። ሚያዝያ /2017 ዓ/ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጅ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ በኢትዮጵያ የአውስትራሊያ አምባሳደር በዶ/ር ፒተር ሀንተር እና በአውስትራሊያ የአየር ንብረት ለውጥ ካውንስለር ሚ/ር ዳንኤል ፊዘርስቶን የተመራ ቡድን ጋር የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ ምን እየተሰራ እንዳለና ምንስ ይጠበቃል በሚሉ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በኢነረጂ ዘርፍ ሙሉ በሙሉ ታዳሽ ሀይልን በመጠቀም፣ ንጹህ የማብሰያ ቴክኖሎጂን ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ እና እንደ ሀገር ለጎረቤት ሀገሮች በአነስተኛ ዋጋ የኤሌክትሪክ ሀይል ተደራሽ በማድረግ፤ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ40 ቢልዬን በላይ ችግኞችን በመትከል ውጤታማ ስራ እደተሰራ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ድኤታ ገልፀዋል። በተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር በከርሰ ምድርና ገፀ ምድር የውሃ ሀብት ጥበቃና በተያያዥነት በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ እተሰራ ያለውን ስራና የመጣውን ውጤት በውይይቱ የተሳተፉ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የዘርፉ ባለሙያዎች አብራርተዋል ። የአውስትራሊያ ልኡክ አባለትም በሀገር ደረጃና በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የከርበን ልቀትን ለመቀነስና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እተደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው ወደፊት በዘርፉ በትብብር የመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል።

Share this Post