የሺንሽቾ ከተማ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ተጠናቅቆ አገልገሎት መስጠት ጀመረ።

የሺንሽቾ ከተማ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ተጠናቅቆ አገልገሎት መስጠት ጀመረ። ሚያዚያ 29/2017 ዓ/ም የሺንሽቾ ከተማ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ተጠናቆ አገልገሎት መስጠት ጀመረ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የሺንሺቾ ከተማ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት መርቆው አገልግሎት አስጀምረዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው መንግስት የጀመረውን ሥራ የሚጨርስ መሆኑን አስታውሰው፤ በክልሉ በርካታ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን አውስተዋል። ፕሮጀክቱ በመገንባት የተሳተፉ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና ሌሎች አካላትን ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ አመስግነዋል። ውሃ ውድና አላቂ በመሆኑ ህብረተሰቡ ለሚጠቀሙ የንፁህ መጠጥ ውሃ ተገቢ ክፍያ እንዲከፍል እና የተሰሩ ውሃ መሠረት ልማት እንዲጠብቅ አሳስበዋል። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በክልሉ ስኬታማ ስራ መሠራቱን ገልፀው፣ በተሰሩ ስራዎች ትምህርት የሚወሰድበት ነው ብለዋል። ክቡር ሚኒስትሩ አያይዘውም በሺንሽቾ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ መቅረቡ ሌሎች የልማት እድሎችን ይፈጥራል ብለዋል። የመጠጥ ውሃ አቅርቦቱ ለረጅም ጊዜ እንዲያገለግል የከተማው አስተዳደር እና የከተማው ማህበረሰብ ተገቢውን ጥበቃ እንዲያደርጉና የውሃ አልግሎቱ ዘላቂነት ላይ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል። ፕሮጀክቱ ከጣሊያን እና ከፈረንሳይ መንግስታት በተገኘው የገንዘብ ድጋፍ በ197 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባ ሲሆን ከ43 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደርጋል።

Share this Post