የቡኢ ከተማ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ተጠናቆ አገልገሎት መስጠት ጀመረ፡፡

የቡኢ ከተማ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ተጠናቆ አገልገሎት መስጠት ጀመረ፡፡ ሚያዚያ 28/2017 ዓ/ም የቡኢ ከተማ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ተጠናቆ አገልገሎት መስጠት ጀመረ፡፡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ዶ/ር እንዳሸው ጣሰው እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የቡኢ ከተማ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት መርቀው አገልግሎት አስጀምረዋል፡፡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ዶ/ር እንዳሸው ጣሰው ባለፉት የለውጥ ዓመታት ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን መከናወናቸውን ገልፀዋል፡፡ የተሰሩ የውሃ ተቋማትን በመንከባከብና ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ በመፈጸም የተቋሙፕማትን ዘላቂነት ማረጋገጥ ይጠበቃል ብለዋል ። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ አሁን ላይ በኢትዮጵያ ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍልን ባረጋገጠ መልኩ የውሃ ችግር እየተፈታ ይገኛል ብለዋል። ክቡር ሚኒስትሩ አያይዘውም በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ44 በላይ ፕሮጀክቶች በ7.1 ቢሊዮን ብር በሚኒስቴሩና በእግር ድርጅቶች የእየተተገበሩ መሆኑን ገልፀዋል። በተጨማሪም በክልሉ የግድቤን በደጀ እና የጎርፍ መከለከል ስራዎች እየተከናወኑ ነው ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ የተገነባው የውሃ ተቋም በዛለቂነት አገልግሎት እንዲሰጥ በአግባቡ መጠበቅ እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል። የውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቱ 210 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባ ሲሆን ከ35 ሺህ በላይ የከተማውን ህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ።

Share this Post