በሐዋሳ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የአዴሌ ፕሮጀክት የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ በቀጣይ በዘርፉ ለሚሰራው ስራ የጋራ ግንዛቤ በመጨበጥ ቅንጅታዊ አሰራርን ያጎለብታል ተባለ።

በሐዋሳ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የአዴሌ ፕሮጀክት የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ በቀጣይ በዘርፉ ለሚሰራው ስራ የጋራ ግንዛቤ በመጨበጥ ቅንጅታዊ አሰራርን ያጎለብታል ተባለ። ሚያዚያ 27/2017ዓ.ም ( ው .ኢ.ሚ) ለሁለት ቀናት በሐዋሳ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ በቀጣይ በዘርፉ ለሚሰራው ስራ የጋራ ግንዛቤ በመያዝ ቅንጅታዊ አሰራር እንዲጎለብት የጎላ ሚና አለው ሲሉ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ ላይ ተናግረዋል። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ ከኢነርጅ አደረጃጀት ጋር በተያያዘ ከፌደራል ጀምሮ እስከታች ድረስ ወጥ የሆነ አደረጃጀት እንደማይጠበቅና የተጀመረውን ቅንጅታዊ አሰራር አጠናክሮ መቀጠል አዋጭነት እንዳለው ገልጸዋል። ከውይይቱ የተገኘውን ግብዓት በመውሰድ አተገባበር ላይ የሚያጋጥሙ ክፍተቶችን በመሙላት ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚጠበቅም አሳስበዋል። በቀጣይም ተግባር ተኮር የአቅም ግንባታ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉና ከሶላር ጋር በተያያዘ ለሚሰሩ ስራዎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል። የብርሃን ተደራሽነት ለሁሉም (አዴሌ) ፕሮጀክት በባህሪው ውስብስብ ቢሆንም አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በዘርፉ ውጤታማ ስራ እየተሠራ ነው ብለዋል። ባዮ ጋዝን በሚመለከት ሁሉም የጠራ ግንዛቤ ሊኖረው ይገባልም ብለዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በባዮ ጋዝ 5ሚሊየን ቤተሰቦችን ተጠቃሚ ለማድረግ ተግባራዊ የሚደረገው በፕሮጀክት ደረጃ ሳይሆን ከክልል እስከ ወረዳ ባለው መዋቅር በማችግ ፈንድ የሚተገበር መሆኑን ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በግልጽ አስቀምጠዋል።

Share this Post